የፅናት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

የፅናት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜን 03 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ማንሠራራት በሚል መሪ ኃሳብ የ2018 ዓ.ም የጳጉሜ ቀናቶች አከባበር አካል የሆነው የፅናት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በምክትሎችና በአየር ምድቦች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ኮሎኔል ገረመው በርጋ፤ አየር ኃይላችን የጀግኖችን ፅናት ተላብሶ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት፣ ግዳጁን በቁርጠኝነት እና ኃላፊነቱንም በታማኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የፅናት ቀንን ስናከብር በተልዕኳችን እየተጋን በቃላችን እየፀናን መሆን እንደሚገባ ያሳሰቡት ከፍተኛ መኮንኑ፤ አመራሩ በኃላፊነት፣ ሠራዊታችን በዲሲፕሊንና በሙያዊ ብቃት ሁላችንም በአንድነት ለተሰጠን አደራና ለዘላቂ ተቋም ግንባታ ጉዟችን መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የአየር ኃይል የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱ አርጋው በበኩላቸው፤ የፅናት ቀን የትናንቱን የጀግንነት ታሪክ የምናስታውስበት፣ ዛሬ ያለውን የሠራዊታችን ፅናት የምናስቀጥልበት፣ አርበኞችንና ጀግኖችን የምናከብርበት እንዲሁም ለሀገር የገባነውን ቃል የምናድስበት የዕምነትና የአደራ ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ ይታያል ምህረት
ፎቶ ግራፍ ባጫ ለገሠ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤21👍6🥰3🔥1
September 8, 2026 2.9K 1