የፅንፈኛው ቡድን አባላት ለሠራዊቱ እጅ መስጠታቸው ቀጥሏል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም
በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 56 የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው እጅ መስጠታቸውን የ10ኛ ዕዝ መረጃ ከፍል አሳውቋል።
በዕዙ መረጃ ክፍል፣ የዞንና የወረዳዎች የፀጥታ አመራሮች እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች በመቀናጀት ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ለሰራዊታችን እጅ እንዲሰጡ እየተደረገ ባለው ያልተቋረጠ ጥረት በርካታ ታጣቂዎች በተከታታይ እጃቸው እንደሰጡና ዛሬም 56 ታጣቂዎች ክላሽ፣ ኋላቀር መሳርያና ፒፒሲኤች ከነ መሰል ተተኳሹ ይዘው መምጣታቸውን ገልጿል።
ለሰራዊታችን እጃቸው የሰጡ ታጣቂዎች በበኩላቸው በበረሀ ቆይታችን አካባቢውን ከማወክ የዘለለ ጥቅም እንዳልነበረ ገልፀው አሁን ግን ከጥፋት ድርጊታችን ተምረን የመንግስት የሰላም ጥሪ ተቀብለን መጥተናል በማንኛውም ጊዜ ሠላም ለማረጋገጥ እንሠራለን ብለዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30
16
6
4
1September 18, 2026 3.9K 5