ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለአቅመደካማ አረጋዊያን የቁሣቁሥ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 02… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለአቅመደካማ አረጋዊያን  የቁሣቁሥ ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም

የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት መጭው 2019 ዓ/ም አዲሱን ዓመት ምክኒያት በማድረግ በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጠህናን ወረዳ በቀበሌ ተወካይ ለተመረጡ 15 አካል ጉዳተኛና አረጋዊያን የቁሳቁሥ ድጋፍ ማድረጉን የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሐላፊ ኮለኔል ጌቱ ወርቁ ተናግረዋል።

የተደረገላቸው ድጋፍ ብርድ ልብስ ፣ፊኖ ዱቄትና ሥኳር ሲሆን ጊዜያዊ ችግራቸውን እንደሚቀርፍላቸው ጠቅሰው ከራስ በፊት ለህዝብ የሚለውን የተቋማችንን እሴት በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወይዘሪት ሽማጫሽ ውበቱና ወይዘሮ አትክልት ታደሠ ሠራዊቱ በዝናብና በብርድ ሣይታክት ሠላማቸውን ከመጠበቅ በተጨማሪ በየጊዜው ለተቸገሩ ወገኖች ለይቶ በመርዳቱ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ አረቡ ሠይድ
ፎቶግራፍ ጥላሁን ጌታነህ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤25👍4🔥3🥰2
September 7, 2026 3.4K