የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በአዳርቃይ ወረዳ እጅ ሰጡ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 27 ቀን 2018… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በአዳርቃይ ወረዳ እጅ ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

በ10ኛ ዕዝ የመብረቅ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ስንታየሁ ሰይድ እንዳሉት በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ አንጓ አካባቢ ሰላምን በማወክ የአካባቢው ስጋት የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች የሰላም አማራጩ ተቀብለው ለሠራዊታችን እጅ ሰጥተዋል።

በአካባቢው ሠላም ለማሥፈን እና አላሥፈላጊ አካሄዶች መቆም አለባቸው ብሎ በማሠብ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲገቡ በተደረገው ጥረት ቁጥራቸው 12 የሆኑ ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው ሠላምን መርጠው ገብተዋል። ዘገባው የክፍለጦሩ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏5❤4👍1😁1
September 2, 2026 2.3K 1