Channels
Top 100TrendingNew
Categories
CryptoGamingNewsEntertainmentMusicSportsTechGamblingBots and mini appsFinanceBusinessEducationLifestyleHealthTravelAutoFashionJobsDatingDeals and shopping
Stickers
StickersEmojiThemesWallpapers
BotsGiftsTools
Currency
$ USD₽ RUB€ EUR₴ UAH₸ KZT₺ TRYzł PLN₪ ILSAED AEDR$ BRLRp IDRRM MYR¥ JPY₩ KRWCN¥ CNY
Theme
EnglishРусскийEspañolPortuguês (Brasil)ArabicPersianBahasa IndonesiaFrançaisDeutschTürkçeBahasa MelayuItalianoNederlandsO'zbekPolskiБеларускаяУкраїнськаҚазақша한국어中文日本語CatalàSuomiHebrew
ChannelsCategoriesStickersBotsGiftsTools
PremiumWikiGlossaryLegal
NotificationsSettingsLog in

An open web layer over public Telegram — search, stats and channel reading right in your browser, no account, no install.

Not affiliated with Telegram FZ-LLC; all data comes from public sources.

Catalog

Top channelsCategoriesCountriesSearch

Content

StickersEmojiGiftsThemesWallpapers

Help

ToolsWikiGlossaryBlockchainSafetyPremiumAdvertisersAdvertising
© 2026 TG.ME · G.Media network· Updated 08/31/2026 · v0.2.0 · b1444ad
PrivacyTermsDMCA & complaintsReport a violation

ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ

@Eyosc1 · 242.2K subscribers

EducationCreated in 2017

🛑የደራሲያን፣ ገጣሚያን፣ ከያኒያን እና የተለያዩ ግለሰቦች የሕይወት ታሪክና ሥራዎች፤ #ወጎች፣ #ግጥሞች፣ #ልብ ወለዶች፣ #የፍልስፍናና የስነ-ልቦና ፅሁፎች፣ #ተረትና ምሳሌዎች #ትረካዎች በድምፅ ያገኛሉ ። 🛑የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks ለማስታወቂያ ስራ ☎️+251933324708 +251922788490 📩 • @Eyos18

Open in Telegram

Information

Username@Eyosc1
CreatedNovember 2, 2017
Linkt.me/Eyosc1
Paid messages1
Paid reactionsAvailable
242.2K
Subscribers
19.3K
Average reach
—
Engagement (ER)
+0.3%
Growth over 24 days
Full stats →
PostsMediaStatsSimilarReviews
⌘K
Newest first
Newest firstOldest first
Share channel “ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ”

The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.

tg.me/go/Eyosc1

Is this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →

Channel history

Channel created November 2, 2017per Telegram

We have been tracking it since July 17, 2026

In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.

We show only what we have seen ourselves.

PostsMediaStatsSimilarReviews

Who advertises in @Eyosc1

16 advertisers placed 16 creatives in this channel · est. CPM $5–15.

@mrkinggold555_2652a1@forexxauusdmarkets99811@misconlifestyle1@ore_na_ah781@tradelearningacademy1
All ads and analytics in TG Ads Spy →Channel stats and history →
Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....
29Aug 30
❗️
❗️
❗️
❗️
❗️
❗️
❗️
❗️


የአንበሳ ልጅ ምን ይባላል?

ቀድመው ለመለሱ 5 ሰዎች የ500 ብር ካርድ ይሸለማሉ።
20Aug 30
የምትወዳትን ልጅ ስታገኝ የምታወራው ይጠፋብሀል ⁉️


👉ከስር ነበብ ነበብ አርገህ ፍጠንባት‼️

⚜ወንድ እስከሆንክ ድረስ ቀልጠፍ ማለት አለብህ‼️


😋 ከስር view የሚለውን በመጫን ያገኙታል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
45Aug 30
#አንድ ቅዳሜ ጠዋት በአሜሪካን ኦሪገን የምትኖረው ክሪስታል ሊሪ ስጋ ለመግዛት ወደ አንድ የስጋ ገበያ ትሄድና ሆንዳ መኪናዋን ከሱቁ መግቢያ 15 ጫማ ያህል ርቀት ላይ ታቆማለች።

የሚያስፈልጋት ስጋ እና አንድ ጋሎን ወተት ብቻ ስለሆነ አልቆይም በማለት አስባ ፣ የመኪናዋን ሞተር ሳታጠፋ በሮቹን ከፍታ የአራት አመት ህፃን ልጆን ከኋላ ባለው መቀመጫ ትታው ወደ ሱቁ ትገባለች።

ሱቁ ውስጥ እንዳለች አንድ ሌባ ያልተቆለፈ፣ ክፍት መኪናውን ውስጥ ገብቶ መኪናውን እየነዳ ሲሄድ አንድ የሱቅ ሰራተኛ ተሽከርካሪው ሲወጣ አይቶ ወዲያውኑ ለክሪስታል ያሳውቃል ።

መጀመሪያ ላይ ሌባው ከኋላው አንድ ትንሽ ልጅ እንደተቀመጠ አላወቀም ነበር። ህፃን ልጅ በመኪና ውስጥ እንዳለ ካስተዋለ በኋላ ዞሮ መኪናውን ከሰረቀበት ወደ ገበያ ይመለሳል ።

የመኪና ሌባው የልጁን እናት ክሪስታልን "እንዴት ልጅሽን በተከፈተ መኪና ውስጥ ብቻውን ጥለሽ ትሄጃለሽ! ህፃናት ልጆችን የሚሰርቁ ሌቦች እንዳሉ አታውቂም ?" ሁለተኛ እንዲህ አታድሪጊ በማለት በቁጣ ገሰጻት ።

ሌባው ህፃን ልጁን ለእናቱ ለክሪስታልን በሰላም ከመለሰ በኋላ እንደገና ወደ መኪናው ገብቶ በፍጥነት እየነዳ ከአካባቢው ተሰወረ።

በኋላ ላይ ፖሊሶች በርካታ ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው በፖርትላንድ የተሰረቀችው መኪና እንዳገኙና ተጠርጣሪ ሌባውን በፍለጋ ላይ እንደሆኑ ሪፖርት አድርገዋል ።


#Share #Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡


❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

❇️ግሩፑን ለማግኘት
          👇👇

https://t.me/Mtshaf_bicha
🙏አሰተያየት ካላችሁ👇
                 @Eyos18  አድርሱን
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
2.2K 10Aug 21
📚ፈውስ የራቀው ሰው

አለን ኤስ በአንድ ትልቅ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ድርጅት ውስጥ የመስክ ተወካይ በመሆን ያገለግላል። ይህ ሰው ባለቤትና አራት ልጆች ያሉት ቢሆንም ከሌላ ሴት ጋር ድብቅ የፍቅር ግንኙነት መስርቷል።

ወደኔ ሲመጣ፣ ፊቱ ላይ ፍርሃት ይነበብበት ነበር፣ ቁጣ ቁጣም ይለዋል። እንደገለፀልኝ የእንቅልፍ እንክብል ካልወሰደ እንቅልፍ በዓይኑ አይዞርም። ከፍተኛ የደም ግፊት እና ሐኪሙ ያላወቀችለት ሌሎች የውስጥ ሕመሞች ነበሩበት። በዚያ ላይ ከልክ በላይ ይጠጣል።

ብዙም ሳይቆይ ለመረዳት እንደቻልኩት፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤው በውስጡ ያለ ስር የሰደደ የሃጢያተኛነት ስሜት ነው። ያደገበትን ሃይማኖቱን እጅግ በጣም ያከብራል፣ ይፈራል። በዚህ የተነሳ የጋብቻ ቃል-ኪዳኑን በማፍረሱ ውስጡ በወንጀለኛነት ስሜት እየተለበለበ ነው።

ይህንን የአዕምሮ ቁስል እንዲጠግግ እና እንዲሁም ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ብሎ አዘውትሮ የሚወስደው መጠጥ ችግሩን ከማባባስ በቀር የፈየደለት አንዳችም ነገር አልነበረም። ነገሩ እሳትን በቤንዚን ለማጥፋት እንደመሞከር ነው።

ይህ ሰው ለምን ፈውስ ራቀው?

አለን ስለ አዕምሮአችን ገለፃ ሳደርግለት በሚገባ አዳመጠኝ። ችግሩንም ረጋ ብሎ አሰበው። በመጨረሻ ይህን ድብቅ ግንኙነቱን ለማቆም ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የመጠጥ ሱሱም ቢሆን ሳይረዳ ከራሱ ለመሸሽ ያደረገው ሙከራ እንደሆነ ተረዳ።

ድብቁ አዕምሮው ውስጥ የተሰነቀረው ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ተመንግሎ እስካልወጣ ድረስም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያገኝ ተረዳ። ይህም በውስጡ የመተማመን መንፈስ ፈጠረለት። ገንቢ የሆነው ሃሳብ አፍራሽ የሆነውን አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ደመሰሰው።

በመጨረሻ ይህ ሰው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ለመላቀቅ በቃ። .....

ከተጠናወተን ጎጂ ልማድ ለመላቀቅ ጥልቅ ፍላጎት ካለን፣ ሃምሳ አንድ በመቶ ፈውስ እንዳገኘን ይቆጠራል። ይህን ጎጂ ልማድ ለማቆም ያለን ፍላጎት፣ ለመቀጠል ካለን ፍላጎት የበለጠ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ብዙም ከባድ አይሆንብንም።

በአዕምሯችን መላልሰን የምናስበው ነገር የመጉላት ባህርይ አለው። በመሆኑም፦
→ ከጎጂ ልማድ የመላቀቅን ነፃነትንና የአዕምሮ ሰላምን መላልሰን እናስብ።
→ አትኩሮቶቻችንን ሁሌ በዚህ አዲስ አቅጣጫ እናድርግ።
→ ይህን ስናደርግ ቀስ በቀስ የነፃነትና የሰላም ስሜት በመላ አካላችን እየተሰማን ይመጣል።
→ ይህም በድብቁ አዕምሮ ወዲያው ተቀባይነት በማግኘት በነባራዊ ሕይወታችን ውስጥ መገለጥ ይጀምራል።

ድብቁ አእምሮ በአእምሮአችን ውስጥ ያለ እንቅፋትን ያስወግዳል!

📒አእምሮን በብቃት በመጠቀም
     መልካም ሕይወትን የመምራት
             ቁልፍ ምስጢራት
     (The Power of Your
     Subconscious Mind)
✍ Joseph Murphy
ትርጉም ➢ እስክንድር ስዩም ዮሐንስ
📕161 - 163
📗አራተኛ እትም - ጥቅምት 2003


#Share #Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን

❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/uIFPaM1OTCs?si=USJVeK-kLvqmxfst

❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

❇️ግሩፑን ለማግኘት
          👇👇

https://t.me/Mtshaf_bicha
https://t.me/piyasa188
   
🙏አሰተያየት ካላችሁ👇
                   @Eyos18  አድርሱን
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
4K
#የፈጣሪ_መጠን_ምን_ያህል_ነው?🖍
Ⓜ️አንድ ልጅ አባቱን "የፈጣሪ መጠን ምን ያህል ነው?" ሲል ጠየቀው።

Ⓜ️ከዚያም አባትየው ወደ ሰማይ አሻቅቦ አውሮፕላን ተመለከተና ልጁን "የዛ አውሮፕላን መጠን ምን ያህል ነው?" ሲል ጠየቀው።

Ⓜ️ልጁም "በጣም ትንሽ ነው። እምብዛም አይታይም" ብሎ መለሰ።

Ⓜ️አባትየው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ወሰደውና እየተጠጉት "እና አሁን የዚህኛው መጠን ምን ያህል ነው?" ሲል ጠየቀው።

Ⓜ️ልጁ "ዋው አባቴ ይህ ግዙፍ ነው" ብሎ መለሰ።

Ⓜ️አባቱ "ፈጣሪም እንዲህ ነው። መጠኑ በአንተና በእርሱ መካከል ባለው ርቀት ይወሰናል። ወደ እሱ በቀረብክ መጠን እርሱ በህይወትህ ውስጥ ግዙፍ ይሆናል" አለው።

#ደዊት_ድሪምስ..📖🖍

#Share
#Share #Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን

❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/uIFPaM1OTCs?si=USJVeK-kLvqmxfst

❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

❇️ግሩፑን ለማግኘት
          👇👇

https://t.me/Mtshaf_bicha
https://t.me/piyasa188
   
🙏አሰተያየት ካላችሁ👇
                     @Eyos18  አድርሱን
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
4.6K 35Jul 30
በቻይና ሲቹዋን ግዛት ውስጥ በምትገኝ አንዲት ጸጥተኛ መንደር፣ ዣንግ ሊዮንግ የተባለ አባት ማንኛውም ወላጅ ሊያጋጥመው የማይገባውን እጅግ አስከፊ ውሳኔ ወስኗል። የሁለት ዓመቷ ሴት ልጁ ዣንግ ዢንሌይ፣ "ታላሴሚያ" በተባለ ከባድ የደም በሽታ ትሰቃያለች፤ ይህ በሽታ ሰውነቷ በቂ ሄሞግሎቢን እንዳያመነጭ ያደርገዋል።

​ለሁለት ዓመታት ሙሉ ወላጆቿ ለልጃቸው ህይወት ታግለዋል። ከወዳጅ ዘመድ በመበደር ከ12,000 ዶላር በላይ ለህክምና አውለዋል። ነገር ግን ገንዘባቸው አለቀ፤ አማራጫቸውም ተዘጋ።

​ሌላ ምንም ማድረግ ሲያቅተው፣ ዣንግ አንድ ማንም ሊያስበው የማይችለውን ነገር አደረገ። የልጁን መቃብር በራሱ እጅ ቆፈረ።

​ይህንን ያደረገው በተስፋ መቁረጥ ሳይሆን... ከልክ ያለፈ ፍቅር የተነሳ ነው።

​አሁን በየቀኑ ወደዚያ ቦታ ይወስዳታል ልክ እንደማንኛውም አባትና ልጅ በፓርክ እንደሚጫወቱት፣ እሷም በመቃብሯ አጠገብ ትጫወታለች።

​ይህንን የሚያደርገው ሊያስፈራራት ሳይሆን፣ ያ ቀን ሲመጣ ቦታው ለእሷ እንግዳ እንዳይሆንባት ነው፤ ቦታው የለመደችው፣ የምታውቀውና ሰላማዊ እንዲመስላት ነው።

​አባትየውም እንዲህ ይላል፦ "እሷ የምታርፍበት ቦታ ይሄ ነው። እኔ ማድረግ የምችለው ብቸኛው ነገር በየቀኑ ከጎኗ መሆን ብቻ ነው..."

​ልጅቷ ትስቃለች፣ ትጫወታለች። የዚያ ቦታ ትክክለኛ ምንነት ምንም እውቀት የላትም።

​አባትየው ግን ያውቀዋል። ሆኖም ግን፣ ገና ከእሷ ጋር የቀሩትን ጥቂት ጊዜያት በአግባቡ ለመጠቀም፣ በየቀኑ መጥቶ ያንን ቦታ ከልጁ ጋር ይጋራል።

​እውነተኛ የፍቅር መገለጫ... አንዳንድ ጊዜ ፍቅር ከምንገምተው በላይ ዋጋ ያስከፍላል። 💔🥀


#Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

https://youtu.be/uIFPaM1OTCs?si=XPNVCGzU2fgah2GG
3.6K 34Jul 22
Live stream started
Jul 14
🤔ደስተኛ የነበረው ልጅ ድብርታም፣ብቻውን የሚያዝን እና ዝምተኛ ሆነ ምክንያቱ ደግሞ እናቱ ሞታ አባቱ ሌላ አግብቶ ከእንጀራ እናት ጋር መኖር በመጀመሩ ነበር።

አንድ ቀን አባቱ ልጁን ጠራውና "በእናትህ እና በእንጀራ እናትህ መሃል ልዩነት አለ?" ብሎ ጠየቀው። ልጁም "አዎ" ብሎ መለሰ፡፡ አባቱም "ልዩነታቸው ምንድን
ነው?" ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡ ልጁም "እናቴ ውሸታም ነች፡፡ የእንጀራ እናቴ ግን ቃሏን ትጠብቃለች" ሲለው ያልጠበቀውን መልስ ያገኘው አባትም በመገረም
"ምን ማለትህ ነው?" ይለዋል ፡፡

ልጁም እንዲህ አለ "እናቴ እያለች ጓደኞቼ ቤት እየሄድኩ እጫወት ነበር።እናቴም በተደጋጋሚ ጓደኞቼ ቤት ሄጄ መጫወቱን
እንድተው ካልተውኩ ግን ምግብ እንደማትሰጠኝ ትነግረኝ ነበረ፡፡ ሆኖም ግን እኔን ቤት ውስጥ ስታጣኝ የምትሰራውን ስራ አቁማ እኔን ፍለጋ ትወጣና ስታገኘኝ
ወደ ቤት ወስዳ ምግብ ትሰጠኝ ነበር፡፡ የእንጀራ እናቴ ግን ቃሏን ታከብራለች። ለዛም ነው ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ ያልበላሁት፤ እርቦኛል፣ እናቴም ናፍቃኛለች እናም የማለቅሰው ስለከፋኝ ነው" እያለ ማልቀስ ጀመረ፡፡ አባት የሚያደርገው ግራ ገባው እና አብሮት ያለቅስ ጀመር...
***

❤️,እናትን ማን ይተካታል?
#እናትነት እውነት ይልሀል❤️

#Share
#Share #Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን

❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Eb7GSEtReo0?si=xnW1Fqjr0ezyZ2xo

❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

❇️ግሩፑን ለማግኘት
          👇👇

https://t.me/Mtshaf_bicha
https://t.me/piyasa188
   
🙏አሰተያየት ካላችሁ👇
                      @Eyos18  አድርሱን
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
5.8K 34Jul 10
Live stream started
Jul 6
#ከጭንቀት_ለማምለጥ

ከዕለታት ባንዱ ቀን...በዚህች ዓለማዊ ህይወት ሃሳብና ጭንቀት የተጨናነቀ ሰው ወደ አንድ ጥበበኛ አዛውንት ጋር መጣ። እናም እንዲህ ተወያዩ......

ባለ ጉዳዩ ፡- “ ወደ እርሰዎ ዘንድ የመጣሁት ካለሁበት የህይወት አጣብቂኝ መውጣት የምችልበትን መፍትሄ ፈልጌ ነው ። ”

ጠቢቡ ፡- “ ሁለት ጥቄዎችን ልጠይቅህ እሻለሁ ። ”

ባለ ጉዳዩ ፡- “ ይጠይቁ ! ”



ጠቢቡ ፡- “ ወደ ዚህች ዓለም ስትመጣ አሁን ከተጋረጠብህ ችግር ጋር አብረህ ነው  የመጣኸውን ? ”

ባለ ጉዳዩ ፡- “ ኧረ በፍፁም  ! ”

ጠቢቡ ፡- “ጥሩ❗️ ይህችን ዓለምስ ተሰናብተህ ስትጓዝ አሁን የተጋረጠብህን የችግር  ጠቅልለህ ነው እንዴ የምትሄደው ? ”

ባለ ጉዳዩ ፡- “ አይደለም ”

ጠቢቡ ፡- “ ካንተ ጋር አብሮ ያልመጣ እና አብሮህ የማይጓዝ ችግር ይህን ሁሉ ሃሳብና ትካዜ ሊያወርስህ ተገቢ አይደለም ።.....

ጠቢቡ ትንሽ ካሰላሰሉ በኋላ...."ሰማኸኝ የኔ ልጅ....

👉በምድራዊ ጉዳይ ታጋሽ መሆን ይጠበቅብሃል ። ያሻኸውን ታገኝ ዘንድ እይታህን ወደ መሬት ከምታደርገው በረዘመ መልኩ ወደ ሰማይ አሻግረው ።

አሁንም በተመስጦ ተሞልተው "እምምምም.." ካሉ በኋላ

👉 ልጄ ሲሳይህ የተወሰነ ነው …

👉"ላንተ ነው !"የተባለውን አንተ ብቻ ነህ የምታገኘው …

👉ላንተ ያልሆነው ፈፅሞ ያንተ አይደለም ።

ትንሽ በአትኩሮት ካሰላሰሉ በኋላ.....

👉 ልጄ ሆይ ምድርን የምትሰናበተው አንተ በፈለከው ጊዜ ሳይሆን እርሱ በወሰነው ወቅት ነው ።

👉ህይወት ህያው እና ሃያል በሆነ ፈጣሪ ቁጥጥር ስር ሆና ሳለ ያንተ በትካዜ መቆራመድ ፋይዳ የለውም ።

👉ሲሳይህ የሚሰፈረው በሰው እጅ ሳይሆን የሲሳይ ጎተራው ልኬት በሌለው ፈጣሪ ነው ።

👉ትላንትን የኖርክበት የህይወት ቀመር ትርፉ ስቃይ ብቻ ከነበረ ዛሬ የምትኖርበትን የህይወት ቀመር ለውጠው ።

......ትንሽ በአትኩሮት ዐይናቸውን ከጣሉበት በኋላ......

👉 የኔ ልጅ ከመሳቀቅ በፈጣሪህ መመካት ይሻላልና ተመካ !!!".......ሲሉ መከሩት❗️

#Share
#Share #Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን

❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Eb7GSEtReo0?si=xnW1Fqjr0ezyZ2xo

❤መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

❇️ግሩፑን ለማግኘት
          👇👇

https://t.me/Mtshaf_bicha
https://t.me/piyasa188
   
🙏አሰተያየት ካላችሁ👇
                      @Eyos18  አድርሱን
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
10.2K 38
6.4K 6Jun 14
​💰 የአይሁዳውያን የስኬት ሚስጥር..
​እንዲህ ያስባሉ 🧠

1.ሰዎች በአንተ ቢስቁብህ ምንም አይደለም፤ ዋናው በአንተ ምክንያት እንዳያለቅሱ መጠንቀቅ ነው።

2.​ፈጣሪ ለሰው ልጅ ሁለት ጆሮ እና አንድ አፍ የሰጠው፣ ከምንናገረው በላይ እንድንሰማ ብሎ ነው።

3.​ድሃ መሆን አያሳፍርም፤ ነገር ግን ስለ ድህነት ሊነገር የሚችል ብቸኛው "ጥሩ" ነገር ይሄው ብቻ ነው።

4.ገንዘብ ቢጠፋ፣ ቢሰረቅ ወይም ቢባክን፤ ጥበበኛ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ "ጌታ ሆይ! በገንዘብ ስለተካኸው (በነፍስ ስላልመጣህ) አመሰግንሃለሁ።"


ስንት ቁጥር ይበልጥ ጠቃሚ ነው?
​👏 – ጠቃሚ ሆኖ ካገኘኸው Like👍 አድርገው!


​
#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏

#ሰናይ ግዜ ይሁንልን❤️

#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6

#Join us @Eyosc1

#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18

 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
11.8K 48May 20
🚨 ታላቅ የማስታወቂያ ቅናሽ አድርገናል 📢

💓በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ🚩

👉 የ" ቻናል ማስታወቂያ "🔺
👉 የ ሙዚቃ ማስታወቂያ🔹
👉 የ ድርጅት ማስታወቂያ🔻
👉 የቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ🔺
👉 የዩቲዩብና የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ🔹
👉 ትሪትመንቶች 🔻
👉 Consultancy🔺
👉 Technology accessories 🔹
👉 ማንኛውም የትምህርት ማስታወቂያ እና🔺
👉 ሌሎችንም ሽያጮች ያስተዋውቁ💡

✅ይሄን ልዩ ቅናሽ በመጠቀም ከ200,000+ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ምርቶን በማስተዋወቅ በእጥፍ ያትርፉ።✅


👮አሁኑኑ ያናግሩን ➡️👇
✅ 𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 ➻@eyos18
☎️+251922788490
9.6K 23May 15
"ይሙት በቃ" በሉት

እሱ ለ'ሱነቱ ባይተዋር ከሆነ፣
          የራሱ ካልሆነ፤
እይታው ካልጠራ፣ ዓላማው ዝል ሆኖ
          ተስፋው ካልሰከነ፣
እየሞቱ መኖር "እሺ" ካለው ቀልቡ
          ለሽንፈት ካደረ፣
መላ ቢስ ከሆነ መላው ከቀጠነ
          መላው ከታሰረ፤
ለምንም - ለምንም - ለምንም ካልበቃ፣
"ይሙት በቃ!" በሉት፣ በቃው ይሙት በቃ፣
በቃ ይሙት በቃ!

📔 ወፌ ቆመች

✍ ወንድዬ አሊ


#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏

#ሰናይ ቅዳሜ ይሁንልን❤️

#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6

#Join us @Eyosc1

#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18

 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
11.3K 30May 2
💚በህንድ በሚገኝ አንድ ቤተ መቅደስ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ከህንፃው ላይ ከዝሆን ቅርፅ ከተሰራ ውሃ ሲያንጠባጥብ በማየታቸው በጣም ተገረመው የነበረ ሲሆን ፤ብዙዎች ቅዱስ ውሃ እንደሆነ አድርገው አምነውበት ነበር።

ያልተለመደውን ነገር በማየታቸው ወደ መለኮታዊ ፣አምልኮና ድንቅ ስራ አድርገው ቆጥረውት ነበር። ለተወሰነ ጊዜ ጎብኚዎች እንደ መንፈሳዊ ወይም እንዲያውም ተዓምራዊ ነገር አድርገው አይተውታል ።

ከዝሆኑ ቅርፅ የሚወጣው ውሃ እውነተኛው ምንጭ በጣም ሚስጥራዊ ሆኖ ተገኘ… ከህንፃው የአየር ማቀዝቀዣ የሚፈስ ውሃ ሆኖ ተገኝቷል ።


#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏

#ሰናይ ግዜ ይሁንልን❤️

#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6

#Join us @Eyosc1

#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18

 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
12.1K 45Apr 22
Live stream finished (6 minutes)
Apr 22
Live stream started
Apr 22
💚ተስፋ ቢስነትን የገደለው ተስፋ!

(አሌክስ አብርሃም)

ይህ ስዕል "The Body of the Dead Christ in the Tomb" የሚሰኝ ሲሆን የሳለው ደግሞ ዝነኛው የጀርመን ሰዓሊ ሃንስ ሆልባይን  ነው። ድሮ ነው የተሳለው ...በ1520 አካባቢ።

​ስዕሉ የሚታወቀው  የክርስቶስን ስቃይ እና ሞት እጅግ በሚያስደነግጥ እና ወደእውነት በተጠጋ አሳሳል (Realism) በመግለጹ ነው። ሰዓሊው የሰውነት መበስበስን እና የሞት አስፈሪነት አሳይቶበታል ።

ስዕሉን ስትመለከቱት ገና ከስዕሉ መጠን ጭንቀታችሁ  ይጀምራል። የሞትን ብቻ ሳይሆን የመቃብርን አስጨናቂነት ያሳያችኋል። እዚህ ቁማችሁ እዛ ኢየሱስ ጋር የተቀበራችሁ እስኪመስላችሁ ትንፋሽ ያጥራችኋል። ረጅም እና ጠባብ (30.5 ሳ.ሜ x 200 ሳ.ሜ) በቃ በጠባብ መቃብር ውስጥ ያለውን ስሜት መታፈን መወሰን ብቸኝነት ፣ መተው እንዲሰማችሁ  ያደርጋል።

ዝነኛው ሩሲያዊ ደራሲ ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ ይህን ስዕል አይቶ ብርክ እንደያዘው ሚስቱ ተናግራለች። እርሱም  "ይህ ስዕል የአንድን ሰው እምነት ሊያጠፋ ይችላል" በማለት በታዋቂው "The Idiot" መጽሐፉ ላይ ጠቅሶታል። እውነት ነበረው.. ከዛ በፊት የኢየሱስ ምስል ሲሳል ሞት እንኳን እንዲያምርበት ተደርጎ፣ በግርማ ሞገስ  በብርሃን አምድ ነበራ። ከፈኑ እያበራ ፣ መቃብሩ ሰፋ ብሎና አጃቢ መለዓክት ከራስጌና ግርጌ ቁመው።  ይሄንኛው ከፍፁም አምላክነቱ ወዲህ ያለውን ፍፁም ሰውነት በፍፁም ሰዋዊ ሞትና የሞት ተፅዕኖ  ነው የሳለው።

​
​በስዕሉ ላይ የክርስቶስ አካል እንደማንኛውም ተራ ሟች ሰው መበስበስ የጀመረ፣ የገረጣ፣ የቆሰለ እና የጠቆረ ሆኖ ነው የተሳለው። ዶስቶቭስኪ "አንድ ሰው ይህን በስጋ የቆሰለ እና የፈረሰ አካል አይቶ እንዴት 'ይህ አካል ተመልሶ ይነሳል' ብሎ ሊያምን ይችላል?" የሚል ስጋት አድሮበታል። ስዕሉ ትንሳኤን ሳይሆን የሞትን ድል አድራጊነት የሚያሳይ ይመስላል።

​​በመጽሐፍ ቅዱስ ትረካ ውስጥ ሞት በትንሳኤ እንደሚሸነፍ ይታወቃል። ሆኖም በሆልባይን ስዕል ውስጥ ምንም አይነት መለኮታዊ ብርሃን፣ መላእክት ወይም የትንሳኤ ፍንጭ አይታይም። ስዕሉ የሚያሳየው ብቸኝነትን፣ ጨለማን እና የመቃብርን ጥብቅነት ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በእምነት ውስጥ ያለውን "ተስፋ" የሚፈታተን ሆኖ አግኝቶታል። ጓድ ዶስቶቭስኪ።

የሆነ ሆኖ ኢየሱስ ይህን አስፈሪ መርገምት አሸንፎ ተነሳ!! ምን ለማለት ነው አይዞን እንደግለሰብ፣ እንደቤተሰብ፣ እንደህዝብና እንደአገር ትንፋሽም ተስፋም የሚያሳጣ ጊዜ ላይ ሆነን ይሆናል፤ ፀሐፊው ሰዓሊው ተንታኙ ተስፋም የለን እያለ ይሆናል። ግን ተስፋ ከማይጨበጥ መላምትም፣ ከተጨባጭ ትንተናም ያለፈ ነገር ነው።  ይሄንኛው ሳምንት በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከመጨረሻው ተስፋ ቢስ ጉዳይም የመጨረሻው ህያው ተስፋ እንደሚወለድ የምናስታውስበት የምስራች ጊዜ ነው!! አይዞን!!

#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏

#ሰናይ ግዜ ይሁንልን❤️

#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6

#Join us @Eyosc1

#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18

 📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
16.2K 41Apr 6
9.6K 14Apr 6
Older posts

Where to next

نينيمار ابن الانبار4.4M subscribers
Open
منمنصة ابن بابل3.4M subscribers
Open
MAMaths By Gagan Pratap
20
Aug 9
Jun 14
2.3M subscribers
Open
MAMaths By Aditya Ranjan - (Vidyagram) 🇮🇳2M subscribers
Open
PAPARMAR SSC1.3M subscribers
Open
ابابن الدورة1.2M subscribers
Open
شبشبكة ملازمنا1M subscribers
Open
شبشبكة المساعد التعليمية1M subscribers
Open

Reviews

0
Log in to leave a reviewLog in

No reviews yet

Be the first to share your experience with this account.

Write a review