ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ የውል ተፈጻሚ ስላለመሆን /Privities of Contract/ 🏛የፍትሐ ብሔር ህግ… — Ethiopian Construction Vacancy & Tender — TG.ME

👉ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ የውል ተፈጻሚ ስላለመሆን /Privities of Contract/

🏛የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1952 “በህግ ተለይቶ የተመለከተ ካልሆነ በቀር ውሎች ውጤት ያላቸው በተዋዋሏቸው ወገኖች መካከል ብቻ ነው”

ውል ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ ተፈጻሚነት እንደሌለው የታመነ ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ፍትሃብሄር ሕግም በአንቀጽ 1952 ላይ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

በዚህም መሰረት ውሎች ልዩ ሁኔታዎች (exceptions) እንደተጠበቁ ሆነው በሦስተኛ ወገኖች ላይ ተፈጻሚ አይሆኑም ማለት ነው፡፡

ታዲያ! ከዚህ መርሆ ተቃርኖ በሚመስል መልኩ መሀንዲሱ እንዴት በአሰሪው እና በሥራ ተቋራጩ መካከል በተደረገ ውል ላይ ጣልቃ ሊገባ ይችላል ፣ ብሎም የተለያዩ ሚናዎች ሊኖሩት ቻሉ የሚሉ ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም ይስተጋባሉ፡፡

🌟መልሱ፦መሀንዲስ የአሰሪው ወኪል መሆኑ በራሱ የተለያዩ በሕግ ፊት ሊጸኑ የሚችሉ ተግባራትን (juridical acts) ሊፈጽም ይችላል እንደ ማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በወጥ ውሎች ላይ እንደተመለከተው የፕሮጀክቱ ተሳታፊ በመሆኑ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ግልጽ ነው፡፡

ለሚወዱት ያጋሩ❤️

@etconp
🥰1🙏1
September 5, 2026 1K 3