አካባቢያችሁን በጥንቃቄ ምረጡ!
“አካባቢ” ማለት በየቀኑ በአስተሳሰባችን፣ በስሜታችን፣ በውሳኔዎቻችን፣ በልማዶቻችንና በባህሪያችን ላይ ተደጋጋሚ ተጽእኖ የሚያደርጉትን ሰዎችን፣ ቦታዎችን እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን አመልካች ነው።
1. ሰዎች
ከእኛ ጋር በተደጋጋሚ የሚያሳልፉ ሰዎች አበረታች ከሆኑ ዓላማችንን ሊያጠናክሩ ይችላሉ፤ ተስፋ አስቆራጭና የሚያዘናጉ ሰዎች ግን ዓላማችንን ሊያዳክሙ ይችላሉ።
2. ቦታዎች
ብዙውን ጊዜችንን የምናሳልፍባቸው ቦታዎች ወይ ለትኩረት፣ ለሰላም፣ ለዲሲፕሊንና ለእድገት ይረዱናል፤ ወይም ደግሞ ለመዘናጋትና ለጊዜ ብክነት ሊያጋልጡን ይችላሉ።
3. ሚዲያና የምንመገበው መረጃ
የምንመለከተው፣ የምንሰማው፣ የምናነበውና በማኅበራዊ ሚዲያ የምንከተለው ሁሉ አካባቢያችን ነው። ይህ ደግሞ ብዙ ነገርን ወደ አእምሯችን በየቀኑ እንድናስገባ ሁኔታውን ስለሚያመቻች በአስተሳሰባችን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል።
ጥራቱን የጠበቀና ከዓላማ አንጻር የሚኖርን ሕይወት ከፈለጋችሁ፣ የምታቀርቧቸውን ሰዎች፣ የምትውሉባቸውን ቦታዎች እና የምትከታተሏቸውን ሚዲዎች ምረጡ!
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

41
23
3September 2, 2026 3.9K 4 19