🤲
አላህን አዘውትሮ የለመነ ወይ ይሰጠዋል: ወይም ይሰጠዋል!!
ነብዩﷺ በተረጋገጠው ሐዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
📚«مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَدْعُو بِدَعْوَةٍ لَيْسَ فِيهَا إِثْمٌ، وَلَا قَطِيعَةُ رَحِمٍ، إِلَّا أَعْطَاهُ اللهُ بِهَا إِحْدَى ثَلَاثٍ:
إِمَّا أَنْ تُعَجَّلَ لَهُ دَعْوَتُهُ،
وَإِمَّا أَنْ يَدَّخِرَهَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ،
وَإِمَّا أَنْ يَصْرِفَ عَنْهُ مِنَ السُّوءِ مِثْلَهَا»
قَالُوا: "إِذنْ نُكْثِرُ"
قَالَ: «اللهُ أَكْثَرُ»
«አንድ ሙስሊም ምንም ዓይነት ወንጀልና ዝምድናን መቁረጥ የሌለበት የሆነ ዱዐ አያደርግም አላህ ከሦሥቱ አንዱ ቢሰጠው እንጂ;
ወይ የጠየቀው ነገር በፍጥነት ይሰጠዋል,
ወይም ምንዳው ለአኼራ ያከማችለታል,
ወይም በዱዐው አምሳያ ችግር ይመልስለታል።»
ሰሓቦች "የአላህ ነብይ ሆይ! እንደዛ ከሆነማ አብዝተን እንለምነዋ" አሉ።
ሸረሱልﷺ «አላህ ዘንድ ያለው የበለጠ የበዛ ነው» አሏቸው።
የዱዐ መስፈርቶችና አዳቦች አሟልቶ ዱዐ ያደረገ የሆነ ሙስሊም አይከስርም ማለት ነው። ወይ ይህ ይሰጠዋል: ወይም ያኛው ይሰጠዋል!!
ደካማ, ስግብግብ, ችኩል ነንና ሁሌም የምንመኘው ቀጥታ ፍላጎታችን እንዲሟላልን ነው: ዑለማዎች ምን ይላሉ መሰላችሁ;
"አላህ ለምነነው የለመንነው ነገር ሳይሰጠን የዱዐው ምንዳ ለአኼራ ያስቀመጠልንን ምንዳ ማየት ብንችል ኖሮ;
አንደኛችንም ዱዐችን ተቀብሎን ፍላጎታችን እንዲሟላ ባልፈለግን ነበር። ምክንያቱም ለአኼራ የሚያስቀምጥልን ዱንያ ላይ ከሚሰጠን እጅግ የተለቀ ነው
🌴🌴🌴