ከትናንት የድህነት ልካችን አንጻር የተሻለ ቦታ ላይ ብንሆንም ዛሬ የተገኙት ስኬቶች እንደ መጨረሻ ማረፊያ ተቆጥረው ወደፊት እንዳንራመድ ሊያግዱን አይገባም።
የጀመርናቸው ተግባራት ዘላቂነት የሚኖራቸው፣ በትንሽ ስኬት ሳንረካ፣ ከብሔርና ሃይማኖት ድንበሮች ተሻግረን ሰው በመሆናችን ብቻ ስንተሳሰር ነው።
አንዱ አካባቢ ሲለማ ሌላው የሚደሰትበት፣ የትዕቢትና የመበላለጥ ስሜትን አውልቀን በመጣል ጤናማ ማህበራዊ ሥነ-ምህዳር መፍጠር የሁላችንም ቀዳሚ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል።
እውነተኛ የሀገር ዕድገትና ትውልድን ማሻገር የሚረጋገጠው በተግባር እንጂ በባዶ ንግግር አይደለም። ዛሬ ላይ የምናፈስሰው ላብ፣ የምናሳየው አንድነትና በጥራት የምንገነባው ማናቸውም ዐሻራ፣ የድህነትን ታሪክ ለልጆቻችን የማናወርስበትን ጠንካራ መሠረት የሚጥል ነው።
ስለሆነም አሁን የጀመርነውን የዜጎችን ክብር የማስጠበቅ፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥና የሀገር በቀል በጎ አድራጎት ባህልን የማጠናከር ጉዞ ይበልጥ በሰው ተኮር ልማት ሥራዎቻችን አጠናክረን በመቀጠል አንገቷን ቀና ያደረገች ኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን ለነገው ትውልድ በጋራ እናሻግር።
EBC














