የመስቀል ሞት ከሌሎች አገዳደሎች የተለየ ነው። ለምሳሌ፣ ተሰይፎ መገደል አስከፊነቱ ያለው የሟቹ ጭንቅላት፣… — Christians Media — TG.ME

የመስቀል ሞት ከሌሎች አገዳደሎች የተለየ ነው። ለምሳሌ፣ ተሰይፎ መገደል አስከፊነቱ ያለው የሟቹ ጭንቅላት፣ አንዳንዴም እጁ ተቈርጦ ለትእይንት መቅረቡ ላይ ነው። (የመጥምቁ ዮሐንስን አሟሟት ያስታውሷል!) በመስቀል የሚገደል ሰው ግን ከነሕይወቱ ነው ለትእይንት የሚቀርበው። ምናልባት ከመስቀል ሞት ጋር የሚወዳደረው ለአራዊት ተወርውሮ መሰጠት ነው። ነገር ግን የመስቀል ሞት የትም ሊፈጸም ሲችል፣ ለአራዊት መወርወር ግን ከተማን ይፈልጋል። በመስቀል መግደል ሌላው ተመራጭነቱ፣ ሰዎችን ለተራዘመና ለከፋ ሥቃይ መዳረጉ ነው።

በወቅቱ የተለያዩ የአሰቃቀል መንገዶች ነበሩ። በአብዛኛው ግን፣ የሚሰቀለውን ሰው መስቀሉ ላይ ማሰርና መቸንከር የተለመደ ነበር። ይህም ዋና ዋና ውስጣዊ ብልቶችን ለጕዳት ስለማይዳርግ ሞቱን ያራዝመዋል። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ፣ የተሰቀለው ሰው ነፍሱ ሳትወጣ ለቀናት እዚያው የሚቈይበት ሁኔታ ይኖራል። ብርቱ አካላዊ ሥቃይን፣ የሕዝብን ስድብና ውርደትን፣ የቀኑን ሐሩርና የሌሊቱን ቁር ችሎ ስቁሉ ሰው እንደ ተንጠለጠለ ይቈያል። ዝንቦች፣ የተለያዩ ነፍሳትና ተባዮች የተሰቀለውን ሰው የተጋጋጠ ጀርባ፣ የቈሳሰሉ እጆችና እግሮችን መውረርና መንከስ ይጀምራሉ። የመስቀል ሰለባ የሆነው ሰው እጅ እግሩ ተወጥሮ ስለሚቸነከር፣ ይህ ሁሉ ሥቃይ ሲደርስበት ምንም ዐይነት ፋታ ማግኛ መንገድ አይኖረውም። ዕርቃንን የመሆን ዕፍረትም አለ። የተሰቀለ ሰው ፍጹም ረዳት የለሽ የመሆን ስሜት ይውጠዋል።

እኛ በቀላሉ የምንተገብረው የመተንፈስ ተግባር እንኳ በመስቀል ላይ ላሉ ሰዎች እጅግ ብዙ ጥረትን የሚጠይቅ፣ እንዲሁም ጣርንና ሥቃይን የሚጨምር ሂደት ይሆናል። በእጃቸው አንጓ ላይ የተንጠለጠለው የሰውነታቸው ክብደት፣ ለመተንፈስ የሚያስችሉ ጡንቻዎቻቸውን ያደክሟቸዋል። ስለዚህ አየር ወደ ውስጥ ለመሳብ በእግሮቻቸው ወደ ታች አጥብቀው በመርገጥ ወይም እጆቻቸውን በመጠቀም ወደ ላይ መንጠራራታቸው ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእግሮቻቸውንና የእጆቻቸውን ቀዳዳዎች ይበልጥ በማስፋት ሥቃያቸውን ያባብሰዋል።

በእጆቻቸው ላይ የተሰካው ምስማር ነርቮቻቸውን በጣጥሶና ጨቍኖ ስለሚይዛቸው ጥቃቅኑ እንቅስቃሴ ሳይቀር ሥቃይን ይፈጥራል፤ በቃላት የማይገለጽ እጅግ ከባድ ሥቃይ። (እንዲህ ዐይነቱ ሕመም በሕክምና ስሙ Causalgia ይባላል። በ1ኛው የዓለም ጦርነት በፈንጂ ፍንጣሪ (shrapnel) እጃቸውን የተመቱ ወታደሮች ‘ሞርፊን’ (morphine) እንኳ የማያስታግሠው ሕመም ነበራቸው።) በዚህም ላይ ከሙቀቱ፣ ከድካሙና ከደም መፍሰሱ የተነሣ እጅግ ለከፋ የውሃ ጥማት ይዳረጋሉ። የጡንቻዎቻቸውን መኮማተርና መዛል፣ የነርቮቻቸውን መበጣጠስ፣ እንዲሁም የተተለተለው ጀርባቸው ከመስቀሉ ዕንጨት ጋር ሲፋተግ የሚፈጥረውን ሕመም ሁሉ በአንድነት ማሰብ ያስፈልጋል። ከታች ሆነው የሚሳደቡና ምራቅ የሚተፉባቸው ሰዎችም ይኖራሉ።

በዚህ ወቅት ሞት በረከት ነው፤ ግና ቶሎ አይመጣም። የሚሰቀሉ ሰዎች በአብዛኛው በመስቀላቸው ላይ ከ3 ወይም ከ4 ሰዓታት እስከ 3 ወይም 4 ቀናት ድረስ በሕይወት ሊቈዩ ይችላሉ። ነፍስ ያላቸው ሬሶች ሆነው ብዙ ከቈዩ በኋላ ነው የሞትን በረከት የሚያገኙት። ስቅለት፣ በተቻለ መጠን የስቁላንን ሥቃይ ማብዣና ማራዘሚያ መንገድ ነው። ከየቱም ዐይነት ዘመናዊ የሞት ፍርድ ማስፈጸሚያ መንገድ ጋር ሲተያይ ዘመናዊዎቹ “ሐዘኔታ የሞላባቸው” ናቸው።

የተሰቀለው ገጽ 32-33።

https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid02wVxaJpodRKJcDZ9Ye6DEvABrREQTtW8cWQVqeiKWDHWotjESJ6tSttf9s8oqqpeSl
Facebook
ምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpit
የመስቀል ሞት ከሌሎች አገዳደሎች የተለየ ነው። ለምሳሌ፣ ተሰይፎ መገደል አስከፊነቱ ያለው የሟቹ ጭንቅላት፣ አንዳንዴም እጁ ተቈርጦ ለትእይንት መቅረቡ ላይ ነው። (የመጥምቁ ዮሐንስን አሟሟት ያስታውሷል!) በመስቀል የሚገደል ሰው ግን ከነሕይወቱ ነው ለትእይንት የሚቀርበው። ምናልባት ከመስቀል ሞት ጋር የሚወዳደረው...
April 8, 2026 30