ትውስ ሲለኝ የጌታዬን ፍቅር ያደረገልኝ በጎልጎታ ከአገር ወደ አገር በመንከራተት ፀሐይና ውርጭ ሲፋረቁበት… — Christians Media — TG.ME

ትውስ ሲለኝ የጌታዬን ፍቅር
ያደረገልኝ በጎልጎታ
ከአገር ወደ አገር በመንከራተት
ፀሐይና ውርጭ ሲፋረቁበት

ይሁዳ ሸጦት ጴጥሮስ ሲክደው
ተከታዮቹም ጥለውት ሲሸሹ
የፊጥኝ ታስሮ ለፍርድ ሲነዳ
ጥፊ እና ግርፉ ሲወርድበት

ትዝ ይለኛል ያ መድኅኔ
በእንጨት ላይ የሞተው ስለ እኔ
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ


አልራሩለትም አስረው ሲገርፉት
ያን መልከ መልካም ሩኅሩኅ ፈጠሪ
የማይችለውን መስቀል አስይዘው
መድኅናቸውን ለፍርድ ሲወስዱ

ሲጮህ ሲያነባ በጣር ተከቦ
በደም ላብ ባሕር ሆኖ ሲያነባ
ሲወድቅ ሲነሳ አባ አባ ሲል
ተሠቃየልኝ ነፍሱ እስክትዝል


ይረሳኛል ወይ ያ የጣር ጊዜ?
መድኀኒቴን የተሳለቁበት
ከመስቀል ውረድ ራስህን አድን
እያሉ ጠላቶች ሲያሾፉበት

ጨለማ ውጦን የነበርነውን
እኛን ለማዳን ከክብሩ ወርዶ
የዓለምን ኀጢአት ያስወገደውን
ታላቁን መድኅን ነፍሴ አትረሳውም
—————————————
ዘማሪ፡ አዲሱ ወርቁ
አልበም፡ ቁጥር 1 - የመስቀሉ ፍቅር
ትራክ፡ ትዝ ይለኛል
ትዝ ይለኛል
April 10, 2026 36 3