Bemnet Library: post #7899 — TG.ME

አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ?

እኔ የእናንተ የቅርብ ጓደኛ ነኝ እንበል....ከዛ በእናንተ ሠርግ ቀን ምንም ባልሰራቹት ወንጀል ለ14 ዓመታት እንድትታሰሩ አደረኩ።

ከዛም ልታገቧት የነበረችውን ሴት ወስጄ ራሴ አገባኋት።አስቡት እናንተም አሳስሬ ፍቅረኛችሁንም ድል ባለ ሠርግ አገባኋት።ከዚህ በኃላ ታሪኩ ሲቀጥል እንደኔ የተሳካለት ሰው ያለ አልመሰለኝም።በቃ በየቀኑ ድግስ ነው፤መዝናናት ነው፤እንዴት ብዬ ልንገራችሁ በጣም ዝነኛ ሆንኩ።ግን ይሄንን ሁሉ ሳደርግ እናንተ በጭለማ እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃያችሁ ነበር።

አሁን ጥያቄዬ ከእስር ቤት ብታመልጡ ምን ታደርጉኛላችሁ?  ማለት ዝም ትላላችሁ? መቼስ 14 ዓመት ሙሉ በእኔ መታሰራችሁና ፍቅረኛችሁ ከእኔ ጋር እንደነበረች ስታስቡ የምትሰቃዩ ይመስለኛል።

ብቻ መጽሐፉ "The Count of monte cristo" ይሰኛል።የተፃፈው በኤክሳንደር  ነው።ዋና ገፀ ባህሪው ኤድመንድ ይባላል።በጓደኞቹ ሴራ ምክንያት በሰርጉ ቀን ይታሰራል፤መታሰር ብቻ ሳይሆን ፍቅረኛውም ትወሰድበታለች።ነገር ግን እስርቤት ለ14 ዓመት ከታሰረ በኃላ አምልጦ የከዱትን ጓደኞቹን ለመበቀል አዲስ ሰው ሆኖ ይመጣል።

በአማርኛ ይለቀቅ?

📚 @Bemnet_Library
18❤123👍52😱5✍3😢2🤝1
August 21, 2026 13.7K 23 22