#ምድረገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወደረው አራተኛ ክለብ ሆኗል!! #በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ38ኛ ሳምንት ላለመውረድ በተለያዩ ሦስት ሜዳዎች ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ሸገር ከተማ በቢኒያም ፍቅሬ ብቸኛ ጎል 1ለ0 በሆነ ውጤት ምድረገነት ሽረን በመርታቱ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊጉ የወረደ አራተኛ ክለብ ምድረገነት ሽረ ሆኗል። #በ2009 በአሁኑ የክለቡ አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ አማካኝነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው እና ከሰሜኑ ጦርነትም በኋላ ባለፈው የውድድር ዘመን መመለስ የቻለው ቡድኑ በሰበሰበው 42 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ መውረዱን አረጋግጧል። #በሌሎች ጨዋታዎች አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን 3ለ2 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር 1ለ1 መቋጨታቸውን ተከትሎ አዳማ እና ወልዋሎ ለከርሞ በሊጉ መሰንበታቸውን አረጋግጠዋል።
July 2, 2026 45