ChatGPT የሰራተኞችን የስራ ወሰን እና ሀላፊነት እያሰፋው መሆኑን አዲስ ጥናት ይፋ አደረገAxios እንደዘገበው የOpenAI አዲስ ጥናት ከ800,000 በላይ የአሜሪካ ኩባንያዎችን የቻት መልእክቶች በመመርመር ሰራተኞች ኤአይን እንዴት እንደሚጠቀሙበት አሳይቷል። እንደ ኢሜይል መጻፍ እና መርሃ ግብር ማስተካከል ያሉ የተለመዱ ስራዎች ከተቀነሱ በኋላ 44% የሚሆኑት ጥያቄዎች የሌላ ሙያ መስክ ስራዎችን የሚያካትቱ ሆነው ተገኝተዋል ይህ አሰራር ኩባንያዎች የሰራተኞቻቸውን የስራ ወሰን እንዲያሰፉ፣ ተጨማሪ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ እና የባለሙያዎችን የቁጥጥር ደረጃዎች እንዲዘረጉ ያስገድዳቸዋል አጠቃላይ ሰራተኞች የባለሙያዎችን ስራ ለመሞከር እድል የሚያገኙ ሲሆን ውስብስብ ነገሮች ሲያጋጥሙ ብቻ ወደ ዋና ባለሙያዎች መምራት ይቻላል ይህ መረጃ ሰራተኞች ኤአይን ተግባራዊ እያደረጉበት ያለውን መንገድ የሚያሳይ እንጂ የስራ እድል መቀነስን ወይም የባለሙያዎችን መተካት የሚያረጋግጥ አይደለም @AddisIntelt.me/Addisintelligence/46412July 28, 2026 32