Addis Intelligence: post #15243 — TG.ME

✴️ OpenAI ከ13 እስከ 17 ዓመት ለሆኑ ታዳጊዎች የተዘጋጀ የተለየ የ-ChatGPT model ይፋ አደረገ

➡️OpenAI ለታዳጊዎች (Users aged 13–17) ተብሎ የተዘጋጀ ልዩ የ-ChatGPT አሰራር ያስተዋወቀ ሲሆን ዓላማውም ዝም ብሎ መልስ ከመስጠት ይልቅ ተማሪዎች ነገሮችን በትክክል እንዲማሩ እና እንዲገነዘቡ (Study Mode) ለማስቻል ነው። አዲሱ አሰራር ጠንካራ የደህንነት ቁጥጥሮችን ለእድሜ የሚመጥኑ ምላሾችን እና የወላጅ ቁጥጥር (Parental controls) አማራጮችን ያካተተ ነው።

➡️ወላጆች አካውንታቸውን ከልጆቻቸው ጋር በማስተሳሰር የ-Quiet hours ገደቦችን ማስቀመጥ የ-Memory እና የ-Privacy ቅንብሮችን ማስተዳደር እንዲሁም በከባድ ሁኔታዎች ላይ የደህንነት ማስጠንቀቂያዎችን መቀበል ይችላሉ። በተጨማሪም OpenAI ቻትቦቱ የታዳጊዎች “የዲጂታል የቅርብ ጓደኛ” እንዳይሆን ገደብ በመጣል ተማሪዎች ከትክክለኛ የሰው ልጆች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖራቸው እና መልሶችን ዝም ብለው ከመቅዳት ይልቅ ራሳቸው አስበው እንዲሰሩ ያበረታታል።

🤩 @AddisIntel
👍1
August 20, 2026 59