OpenAI “Intelligence Age” ለሚባለው የ-AI ዘመን አዳዲስ የፖሊሲ አሰራሮችን ለመፈተሽ ለተመረጡ 14 ገለልተኛ ፕሮጀክቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል። ጥናቶቹ በ-AI ዘመን የሰራተኞች ጥበቃ በ-AI የሚመነጨው ሀብት ፍትሃዊ ተደራሽነት እና ራሳቸውን በራሳቸው የሚያሻሽሉ ሲስተሞች (Recursively self-improving systems) የደህንነት ቁጥጥር ዙሪያ ያተኮሩ ናቸው።
ኩባንያው ከ400 በላይ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የቀረቡለትን ጥያቄዎች ከመረመረ በኋላ አጠቃላይ 1 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ (Grants) እና እስከ 1 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የ-API Credits አቅርቧል። የተመረጡት ፕሮጀክቶች በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት፣ በብራዚል፣ በሲንጋፖር እና በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ሲሆን፣ ለስድስት ወራት የሚቆዩት እነዚህ ጥናቶች ውጤታቸው በ2027 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
