Google DeepMind የምልክት ቋንቋን በቀጥታ ወደ ጽሑፍ የሚቀይር SL2T የተሰኘ አዲስ የ-AI ሞዴል ይፋ አደረገGoogle DeepMind የምልክት ቋንቋን (Sign Language) በቀጥታ ወደ ጽሑፍ የሚተረጉም SL2T (Sign Language to Text) የተሰኘ አዲስ ሞዴል ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም የምልክት ቋንቋ ተጠቃሚዎች የየራሳቸውን ውስብስብ ሰዋሰው እና የ3D አካላዊ እንቅስቃሴዎች በመጠቀም ሃሳባቸውን እንዲገልጹ ያስችላቸዋል። አሰራሩ ካሜራዎችን ወይም ልዩ ጓንቶችን ከመጠቀም ይልቅ በ-MediaPipe Holistic አማካኝነት የሰውነት እንቅስቃሴ ነጥቦችን (Body landmark coordinates) በኮምፒውተር ላይ በቀጥታ በመከታተል ወደ ጽሑፍ ይተረጉማል።ተጠቃሚዎች ሁሉንም ነገር በኪቦርድ ከመጻፍ ይልቅ በተፈጥሯዊ የምልክት ቋንቋ በመጠቀም መፈለግ መልዕክቶችን ማዘጋጀት እና የቀጥታ ውይይቶችን ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ይህም የመስማት እና የመናገር እክል ላለባቸው ሰዎች የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰፋ ነው። @AddisIntelt.me/Addisintel/15231Translate2August 17, 2026 52