ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያሳየችው የንግድ እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ
ኢትዮጵያ ስምምነቱን በቀዳሚነት ከፈረሙና ካጸደቁ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ እ.ኤ.አ ጥቅምት 9 ቀን 2025 በይፋ ንግድ መጀመሯ ይታወሳል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው መረጃ ንግዱ በይፋ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ማዝያ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ባደረገችው የንግድ ልውውጥ፦ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ የላከች ሲሆን፤
ከ8 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ ምርቶችን ደግሞ ወደ አገር ውስጥ አስገብታለች።
በወጪ ንግድ የቅባት እህሎች፣ በቆሎና የኬሚካል ምርቶች ተጠቃሽ ናቸው።
የኢትዮጵያ የወጪ ንግድመዳረሻዎችም ከነበሩበት አራት ወደ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት (ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ጋና እና አልጄሪያ) ከፍ ማለታቸው ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅትም 37 የግል ድርጅቶች በወጪ እና 76 ድርጅቶች በገቢ ንግድ ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ብሏል።
ይህ አህጉራዊ ስኬት ኢትዮጵያ ወደ ዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ተቋማዊና ፖሊሲያዊ ግብዓት የሚፈጥር መሆኑም ተመላክቷል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

9
6
2August 30, 2026 1.8K 1