ተሸንፎም ድርጅቶች ለማስታወቂያ በሩን በሰልፍ እያንኳኩለት ያለው ሴዶ ማርሻል::
በቅርቡ በተደረገው የኤምኤምኤ (MMA) ፍልሚያ በመጀመሪያው ዙር በጆኒ የተሸነፈው ሴዶ ማርሻል፣ ከተሸነፈ በኋላ ያየው ነገር ግን ከድል በላይ የሆነ ድንቅ እድል ሆኖለታል!
ብዙ ጊዜ በተዋጊዎች ዓለም ውድድር መሸነፍ ከስፖንሰሮችና ማስታወቂያዎች መራቅን እያመጣ፣
በሴዶ ላይ ግን የሆነው ተአምር ነው! ሴዶ በተሸነፈ ማግስት ብቻ ከ4 በላይ ትልልቅ ማስታወቂያዎችን የሰራ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ድርጅቶች ማስታወቂያቸውን በእሱ ለማስራት በረጅም ተራ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተሰምቷል!
"መሸነፍ የውድቀት መጨረሻ ሳይሆን ለአዲስ መንገድ በር ከፋች ነው" የሚሉትን ወገኖች እውነት የሚያስመስለው የሴዶ ማርሻል ነገር፣ አሁን ላይ በማህበራዊ ሚዲያ እና በንግዱ ዓለም ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል!
እውነትም ኢትዮጵያ ውስጥ ተሸንፎ እንደ ሴዶ ማተርፍ የትም የለም!
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

14
10
6
1
1August 30, 2026 2.3K 1