የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት በምዕራብ ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎችንና መንደሮችን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ጉዳት እያደረሠ ይገኛል በማለት ለአልጀዚራ በሠጡት ቃል ከሰሱ።
ጌታቸው፣ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ይረዳል በማለት ጭምር መወንጀላቸውን ዜና አውታሩ ማምሻውን ዘግቧል።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከኢትዮጵያ ግዛት እየተነሳ በሱዳን ጦር ሠራዊት ላይ ጥቃት ይፈጽማል የሚለውን የሱዳን ባለሥልጣናት ውንጀላ ያስተባበሉት ጌታቸው፣ ኢትዮጵያ የሱዳንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንደምታከብር ተናግረዋል ተብሏል።
ሱዳን ጦሯን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር ወደሚዋሠነው ብሉናይል ግዛት ደማዚን ከተማ አካባቢ በብዛት እያንቀሳቀሰች መኾኗንም ዘገባው የሱዳን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18
8
2August 29, 2026 4.5K 2