ቢሮው በበጀት ዓመቱ 200 ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተመላከተ።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት ተቋማዊ ዕቅዱን ከክፍለከተማ መዋቅሮቹ ጋር የጋራ አድርጓል።
በዚህም መሰረት በበጀት ዓመቱ ቢሮው በዋነኛነት ከፕሮጀክት አፈፃፀም አንፃር 200 የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎችን አከናውኖ ለአገልግሎት ለማዋል ማቀዱ የተመላከተ ሲሆን የከተማውን መሪ ፕላን መሰረት በማድረግ የ148 ፕሮጀክቶች አዋጪነት ጥናት ለማከናወንም ማቀዱ ተጠቁሟል።
ተያይዞም ለ3100 ስራ ተቋራጮች፣አማካሪዎች እና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የኢንዱስትሪውን ዓቅም ለማሳደግም እነወደሚሰራ ተገልጿል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የ237 ስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ግዢ ለመፈፀም መታቀዱ በቀረበው የዕቅድ ሰነድ ተጠቁሟል።
እንዲሁም ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋትና ለማሻሻል በ472 ፕሮጀክቶች ላይ የክዋኔና ፋይናንሺያል ኦዲት በማከናወን ውጤታማነታቸውን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል ተብሏል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ከከተማው ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ አንፃር ከዘርፉ ተዋንያን ከፍተኛ ስራ እንደሚጠበቅ አንስተው ቢሮው የያዘውን ዓመታዊ ዕቅድ ለማሳካት በማዕከልና በክፍለከተማ ደረጃ የሚገኙ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ እንዲሁም ስራ ተቋራጮችና አማካሪዎችም ጭምር ስራዎችን በተለመደው የ7/24 መርህ እና በጥብቅ ዲሲፕሊን በመከወን የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ከክፍለከተማ ፅ/ቤቶች ጋር በጊዜ ማዕቀፉ ተፈፃሚ የሚሆን የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።
የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 23/2018 ዓ/ም
18
14
2August 29, 2026 2.3K 21








