የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግር ሙሉ በሙሉ የቀረፈችው አዲስ አበባ
መዲናችን አዲስ አበባ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግር ታሪክ እንዲሆን በሰራችው ስራ ከዚህ ቀደም በአንድ ጊዜ 3ሺ ተሽከርካሪ ብቻ የማቆም አቅም የነበረውን ወደ 170ሺ በማሳደግ ተአምራዊ ስራ በጥቂት አመታት ውስጥ ሰርታለች።
በከተማችን አዲስ አበባ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከተማዋን በእጅጉ አጨናንቋት የነበረው የተሽከርካሪ ማቆሚያ ችግር ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ በታላቅ ራዕይና ቁርጠኝነት ወደ ተግባር በመግባት ፤ በጎተራ፣ በቦሌ፣ በየካ እና በቀበና እካባቢዎች ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች በመገንባት የትራፊክ ፍሰት ሙሉ በሙሉ የተቀላጠፉ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ።
እነዚህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናሎች ፕላዛዎች ፣ ሱቆች የህፃናት መጫዎችና ማረፊያ ቦታዋችን ያካተቱ እንዲሁም የሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች እና ካፍቴሪያ ጨምሮ ንፅህ መፀዳጃ ቤት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚሆኑ ቢሮዎች አሟልተው የያዙ ናቸው ።
እነዚህ የፓርኪንግ ስራዎች የትራፊክ ፍሰቱን የሚያቀላጥፉ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለሰው ክብር ቅድሚያ የሚሰጡ እና ተገልጋዩን ከዝናብና ከፀሀይ እንግልት ያሳረፉ ፤በትራፊክ መጨናነቅ ይባክን የነበረውን ጊዜና ጉልበት በመታደግ ለከተማዋ የምቾት ገፅታን ያላበሱ ናቸው ።
ከለውጡ በፊት የነበረውን 3 ሺህ ተሽከርካሪዎች ማቆም አቅም ዛሬ ወደ 170 ሺህ በላይ ከፍ በማድረግ የተሰራው አመርቂ ስራ መንግስት ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር ስለመፈፁሙ ህያው ማሳያ ነው ።
አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ የማድረግ ጉዞአችን በፍጥነት ይቀጥላል!
12
9
4
1August 28, 2026 2.6K









