Abune Gorgorios: post #2011 — TG.ME

Forwarded fromESEsdros S.C
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ8ኛ እና በ6ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት አስመዘገቡ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ካስፈተናቸው የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ውስጥ 99.46% እና 8ኛ ክፍል ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 98.70% የሚሆኑት ከፍተኛ ውጤት ማስመዘገባቸው ተገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ክልል አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ 7 ቅርንጫፍ የሚገኙት የአዋሬ፣ የሲኤምሲ፣ የእግዚአብሄር አብ፣ የቃሊቲ፣ የለቡ፣ የሰንሻይን እና የወይራ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከተፈተኑት 932 ተማሪዎች 927 ተማሪዎች (99.46%) ተማሪዎች ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ማለፋቸው የታወቀ ሲሆን በ8ኛ ክፍል በ7ቱም ቅርንጫፍ ከተፈተኑ 785 ተማሪዎች ውስጥ 775 ተማሪዎች (98.70%) የሚሆኑት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸው ታውቋል፡፡
August 3, 2024 8.8K