ASTU #AASTU የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ!! በ2019… — AAU GENERAL — TG.ME

#ASTU #AASTU

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ!!

በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በኦንላይን በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል፡፡
www.astu.edu.etwww.aastu.edu.et

@AAU_GENERAL
❤1
August 30, 2026 1K 32