አጀንዳ 8፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን የምሳ አበልና የትራንስፖርት ክፍያ መወያየትና የማሻሻያ ውሳኔ ማሳለፍ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ከዚህ በፊት ለዳይሬክተሮች ቦርድና ለስራ አስፈፃሚ አባላት ይከፈል የነበረውን የምሳና የትራንስፖርት አበል ክፍያ ብር 250 እና 200 በቄ አለመሆኑን በማብራራት ማሻሻያ እንዲደረግበት ለጉባኤው አቅርቦል፡፡ ጉባኤውም ማሻሻያው ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን አምኖ የተለያዩ ፕሮፖዛሎች ቀርበው ማለትም ብር 500፣600፣700 እና 800 ድምፅ ተሰቶባቸዋል፡፡ በመጨረሻም በአብላጫ ድምፅ ለዳይሬክተሮች ቦርድና ለስራ አስፈፃሚ አባላት የምሳና የትራንስፖርት አበል ክፍያ ብር 700 እንዲሆን አፅድቆል፡፡
አጀንዳ 9፡ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ውክልና መስጠት
በንግድ ህጉና በአ/ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከዚህ በታች ከፊደል ሀ - ሐ የተጠቀሱት ጉዳዮች የጠቅላላ ጉባኤውን ይሁንታና እውቅና የሚጠይቁ ቢሆንም ከመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ውጭ ሌላ አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ሳይጠራ ቦርዱ እየወሰነ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ይህንን የውክልና ስልጣን በሙሉ ድምፅ ሰጥተነዋል፡፡
ሀ. በአሁኑ ሰዓት ለሚቀጥለው ዓመት የሂሳብ መርማሪ የሚሆን ኦዲተር ለመሾም ባለመቻሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ግልፅና መሰረታዊ የአገልግሎት ግዥ መርሆዎችን ተከትሎ ኦዲተር እንዲሰይምና ሂሳቡን አስመርምሮ ለ3ኛው ጠ/ጉባኤ የኦዲት ሪፖርት እንዲቀርብ እንዲያደርግ፤
ለ. የግንባታ ስራ እንቅስቃሴ ሲጀመር ተግባሩን ቦርዱ ብቻውን መወጣት ስለማይችል ለስራው አስፈላጊ ሰራተኞችን እንዲቀጥርና ከባለድሻ አካላት መካካል ትጉህና አጋዥ የሆኑ ንኡሳን ኮሚቴዎችን እንዲያቋቋም ወይም የኮሚቴ አባላትን እንዲመለምል፤
ሐ. በእያንዳንዱ አባል ስም የተዋጣው ገንዘብ አክሲዮን ማህበሩ ሲመሰረት ከነበረው የግንባር ዋጋ ብር 10,000 (አስር ሽ ብር) በብዙ እጥፍ ከፍ ያለ በመሆኑ የማህበሩን ካፒታል ያሉትን 566 አክሲዮኖች የግንባር ዋጋ በመከለስ እንዲያሳድግ፡፡
December 10, 2025 1.7K