ዘውግ ሪል እስቴትና ንግድ ስራ አ/ማ የ2ኛው ጠቅላላ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ የስብሰባ ቀን፡ ህዳር…

ዘውግ ሪል እስቴትና ንግድ ስራ አ/ማ
የ2ኛው ጠቅላላ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ
የስብሰባ ቀን፡ ህዳር 28/2018
የስበሰባ ቦታ፡ ሳፋ ሪሞል
የስብሰባ ሰዓት፡ ከ3፡00 ጀምሮ
የስብሰባው ተሳታፊዎች፡
ሀ. የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት
• አቶ መስፍን ከተማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፕሬዚዳንት ሰበሰሳቢ
• ዶ/ር ሱራፌል መላክ ም/ሰብሳቢና ስራ አስኪያጅ
• አቶ አለምነህ መኮንን አባል
• አቶ ባምላኩ አበሻ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፀኃፊ
ለ. የአክሲዮን ባለድርሻዎች
• የአ/ማህበሩ አባላት ከዚህ ቃለ ጉበኤ ጋር በተያያዘው የስም ዝርዝር ትይዩ ፊርማችን የተቀመጠው የአክሲዮን ባለድርሻዎች
ስብሰባው ጥሪ የተደረገበት መንገድ፡ በቴሌግራምና ለእያንዳንዱ አባል ስልክ በመደወል ጥሪ ተደርጓል
ሰብሳቢው በአገሪቱ የንግድ ህግ 1243/2013 አንቀጽ 398(1) መሰረት ለጉባኤው መከፈት የሚያስፈልገው ህጋዊ የአክሲዮን ድርሻ ቁጥር መገኘቱን ካረጋገጡ በኋላ ጉባኤው ተጀምሯል።
አጀንዎች
አጀንዳ 1 እና2፡ የስራ አፈፃፀምና ሂሳብ ሪፖርት ማዳመጥ፣ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
አጀንዳ 3፡ ከመጋቢት 29/2013 ዓ/ም - ሰኔ 30/2017 ዓ/ም የለውን የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ተሰርቶ የቀረበውን የኦዲት ሪፖርት ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
አጀንዳ 4፡ የማህበሩን የህንፃ ዲዛይን ለጉባኤው ማስተዋወቅ
አጀንዳ 5፡ ቀጣይ የስራ እቅድ ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
አጀንዳ 6፡ ወርሃዊ እና ልዩ መዋጮ ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
አጀንዳ 7፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መሾም
አጀንዳ 8፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን የምሳ አበልና የትራንስፖርት ክፍያ መወያየትና የማሻሻያ ውሳኔ ማሳለፍ
አጀንዳ 9፡ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ውክልና መስጠት

ወይይትትና ውሳኔ
አጀንዳ 1 እና2፡ የስራ አፈፃፀምና ሂሳብ ሪፖርት ማዳመጥ፣ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
ጉባኤው በአቅራቢዎች የቀረበውን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የሂሳብ ሪፖርት ካዳመጠ በሆላ ሰብሳቢው መድረኩን ለውይይት ክፍት በማድረጉ ተሰብሳቢው የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦችንና ጥያቄዎችን አቀርበዋል፡፡ ለአብነት ያህል ለስራ አመራርና ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የተከፈሉ የምሳ አበልና ለትራንስፖርት የወጡ ወጭዎችን በተመለከተ እንዲሁም አንዳንድ የተፈፀሙ ግዥዎችን በተመለከተ ከማህበሩ ባለድርሻዎች መካከል እማኝ ሁነው እንዲገኙ ሀሳብ ቀርቦል፡፡ በመቀጠልም ለቀረቡት ጥያቄዎች በዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምላሽና ማብራሬያ ተሰቶል፡፡ በመጨረሻም ጉባኤው የስራ አፈፃፀምና የሂሳብ ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

አጀንዳ 3፡ ከመጋቢት 29/2013 ዓ/ም - ሰኔ 30/2017 ዓ/ም የለውን የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ተሰርቶ የቀረበውን የኦዲት ሪፖርት ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
ከመጋቢት 29/2013 ዓ/ም - ሰኔ 30/2017 ዓ/ም የለውን የማህበሩ ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ተመርምሮ ሪፖርቱ በኦዲተሩ በኩል ለጉባኤው ቀርቧል። ኦዲተሩም የኦዲት ውጤቱን በግልፅ እና ፍፁም ሙያዊ በሆነ መንገድ ለአባላት አቅርቦ ዋና ዋና ግኝቶችን እና ምክሮችን በተመለከተ በዝርዝር አስረድቷል።
በመቀጠለም ሰብሳቢው የኦዲተሩን ሪፖርት ለውይይት ክፍት በማድረግ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን፣ ሀሳቦችን እና አስተያየቶችን እንዲያቀርቡ እድል ሰጥተዋል፡፡ ጉባኤውም የተለያዩ ጥያቄዎችን፣ ሀሳቦችን እና አስተያየቶችን ካነሳ በሆላ ሰብሳቢው ለኦዲተሩ ለተነሱ ጉዳዩች መልሽ እንዲሰጡ እድሉን ሰጥቶቸው ምላሻቸው ለጉባኤው አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም ሰብሳቢው ለጉባኤው በተሰጠው ሁለተኛ የውይይት መድረክ ማህበሩ በቀጣይ ዓመት ለሚፈጸሙው ተግባራትና እርምጃዎች ቦርዱ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አዳብሮ ክፍተቶቸን ደግሞ አርሞ ምክረ-ሃሳቦችን በሚገባ እንዲጠቀምባቸው አሳስቧል፡፡ በመጨረሻም ጉባኤው የኦዲት ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

አጀንዳ 4፡ የማህበሩን የህንፃ ዲዛይን ለጉባኤው ማስተዋወቅ
አክስዮን ማህበሩ የሰራውን ሁለት B+G+19+T የሆነውን በውስጡም እስከ ሁለተኛ ፎቅ የንግድ፣ ከሶስተኛ ፎቅ ጀምሮ ባለ ሁለት መኝታ ስፋቱ 100 ካ.ሜ ሆነ ዘመናዊ አፓርታማ በአጠቃላይ 400 ቤቶች የያዘ እየንዳንዱ 2320 ካ.ሜ ላይ የሚያርፍ የህንፃ ዲዛይን በአማካሪ ድርጅቱ ቀርቦል፡፡ በመቀጠልም ሰብሳቢው መድረኩን ለውይይት ክፍት በማድረጉ ተሰብሳቢው የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦችንና ጥያቄዎችን አቀርበዋል፡፡
በመቀጠልም ለቀረቡት ጥያቄዎች በአማካሪ ድርጅቱን በወከሉት እንጂነር ምላሽና ማብራሬያ ተሰቶል፡፡ በመጨረሻም ጉባኤው የህንፃ ዲዛይኑን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

አጀንዳ 5፡ ቀጣይ የስራ እቅድ ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
ጉባኤው በዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን የስራ እቅድ ካዳመጠ በሆላ የመሬት ቁፋሮ (Excavation) ስራው በፍጥነት እንዲጀመር አቅጣጫ ሰጥቶል፡፡ በመጨረሻም ጉባኤው የስራ እቅድን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

አጀንዳ 6፡ ወርሃዊ እና ልዩ መዋጮ ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
ጉባኤው ከላይ በአጀንዳ 5 ያፀደቀውን የስራ አቅድ ማስፈፀሚያ የሚውል ፋይናንስ በዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ ብር 5000 ልዩ መዋጮ እስከ ሰኔ 30 2018 ዓ/ም በሁለት ዙር የሚከፈል ብር 15000 በጠቅላላ ብር 70000 አቅርቦል፡፡
ጉባኤው በቀረበው ፕሮፖዛል እንዲሁም የጉባኤው ተሳታፊዎች ሊሎች አማራጮችን አቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎል፡፡ በመጨረሻም ወርሃዊ ብር 3000 ከታህሳስ 2018 ጀምሮ እንዲሁም ልዩ መዋጮ እስከ ነሃሴ 30 2018 ዓ/ም በሶስት ዙር የሚከፈል ማለትም የካቴት፣ግንቦትና ነሃሴ 2018 ዓ/ም የሚከፈል ብር 10000 በጠቅላላ ብር 56000 እንዲከፈል በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡



አጀንዳ 7፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መሾም
አሁን ያለው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከማህበሩ ምስረታ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያገለገሉ በመሆኑና ያገልግሎት ጊዜያቸው ከማብቃቱም በተጨማሪ የተጓደሉ የቦርድ አባላት በመኖራቸው አዳዲስ የቦርድ አባላትን መሾም አስፈላጊ መሆኑን ሰብሳቢው ለጉባኤው ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሰረት የጉባኤው ተሳታፊዎች የቦርድ አባላትን ሙሉ ለሙሉ መቀየሩ በአ/ማህበሩ የስራ ፍሰትና ቅብብሎሽ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር የተወሰኑት ነባር የቦርድ አባላት አዲስ ከሚመረጡት ጋር ለሁለተኛ ዙር እንዲያገለግሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ እነዚህም፤
1. አቶ መስፍን ከተማ
2. አቶ ባምላኩ አበሻ
ሲሆኑ በአባላት ቀጥተኛ ጥቆማ 3 (ሶስት) አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ከተቋቋመ በኋላ
አዳዲስ የቦርድ አባላትን በተመለከተ 5 (አምስት) ተጠቁመው በተሰጠው ድምፅ መሰረት 3ቱ ክፍተኛ ድምፅ በማግኘታቸው ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው በሰንጠረዠ የቀረበው ግለሰቦች የአ/ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በመሆን ተሹመዋል፡፡
ተ.ቁ ስም ምርመራ
1 አቶ መስፍን ከተማ ነባር
2 አቶ ባምላኩ አበሻ ነባር
3 አቶ ጌጡ ስዩም አዲስ
4 አቶ ጌታቸው አግኝቸው አዲስ
5 አቶ እባቡ ተፈራ አዲስ

የስራ ክፍፍሉን በተመለከተ ቦርዱ ተሰብስቦ በመወያየት ምደባ አድርጎ ለአባላትና ለሚመለከተው ሁሉ እንዲያሳውቅ ጉባኤው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
December 10, 2025 1.3K