የጥቅምት መስክ ነኝ !!
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ
በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን: ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ
ካንጀት ይሁን ካንገት : እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ : መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት: አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ
ከላይ ተሰውሮ : ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ: አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል: ስሩ ከተማሰ!!
የጥቅምት መስክ ነኝ : አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው: ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም: እኔው ነኝ የማውቀው::
(ተከፍተው የተከፉ ለማይመስሉ)
109
37
9
1
1June 24, 2026 10.2K 41