አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል አንድ « በእርግጥ እኔ የምሻው አላህን ፣ መልዕክተኛውን ፣ አንዲሁም ዘውታሪ… — የሳዳት ከማል official የቲክቶክ ሙሀደራዎች ሚለቀቅበት — TG.ME

አዒሻ ቢንት አቡበክር

ክፍል አንድ

« በእርግጥ እኔ የምሻው አላህን ፣ መልዕክተኛውን ፣ አንዲሁም ዘውታሪ የሆነውን የመጭውን ሕይወት መኖሪያ ( ጀነት ) ነው ፡፡ » 【ዓኢሻ 】

የዓኢሻ የሕይወት ታሪክ ሴት ልጅ እንደ ተቃራኒ ፆታዋ አዋቂና የምሁራን መምህር ለመሆን ብቃት እንዳላት ያረጋግጥልናል ። በተጨማሪም ሴት ልጅ በወንዶች አስተሳሰብ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር የአመለካከትና የአመራር ምንጭ መሆን እንደምትችል ፥ አልፎ ተርፎም በእንስትነቷ ለባልተቤቷ የደስታና የምቾት ምንጭ ለመሆን ብቃት እንዳላት ግልፅ ማስረጃነት አለው ።

ዓኢሻ የአንድም ዩኒቨርስቲ ምሩቅ አልነበረችም ። እንዲያውም በዘመኗ ዩኒቨርስቲም አልነበረም ።ግና እንደማር ያንቆረቆረቻቸው ንግግሮቿ በቋንቋ መካነ ጥናቶች እየተጠኑ ነው ።ህግን በሚመለከት የተናገረቻቸው በህግ ኮሌጆች ይጠናሉ ። እንዲሁም ከሕይወት ታሪኳ የሚነበቡ ድርጊቶችዋ የሙስሊሞችን ታሪክ በሚያጠኑ ተማሪዎችና ምሁራን ከሺህ ዓመታት በላይ እየተዳሰሱ ነው ።

ዓኢሻ የዕውቀት ባህር ለመሆን የበቃችው ገና በወጣትነት ዕድሜዋ ነው ።ልጅ ሆና ያደገችው በአዋቂነታቸውና በመልካም ሥነ ምግባራቸው በሚታወቁት በአባቷ በአቡበክር ቤት ነው ።ዐኢሻ በማራኪ ውበቷና በአስደናቂ የማስታወስ ችሎታዋ የታወቀች ነበረች ። በወጣትነት ጊዜዋ የነቢዩ የልብ ተፈቃሪና ታሳቢ ለመሆን በቅታለች ።በሚስትነትም የቅርብ ወዳጃቸው ለመሆን በመታደሏ ሌሎች ሴቶች ሊያካብቱት ያልቻሉትን ዕውቀት ከርሳቸው ለማግኘት ችላለች።

ሙሐመድ ኢብን ፈድሉ

    【 📚ሃያቱ ሶሃባ 】

      “ ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ”

     https://t.me/yetkaru
❤4👍4
July 26, 2026 1.5K 6