"ዛሬ ሐምሌ 22 መልአከ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ይውላል ብርሃኑን ያብራልን🙏
✥ቅዱስ ዑራኤል ከሊቀ መላእክት አንዱ ነው። መላእክት በስማቸው ቅጥያ ኤል የሚል ቃል አለ ይኸውም እግዚአብሔር ማለት ነው። "ዑር" ማለት ብርሃን፤ "ኤል" ማለትም እግዚአብሔር ማለት ነው።ዑራኤል ማለት የብርሀን ጌታ፣ የብርሀን አምላክ ማለት ነው።
✥ የሰማይን ሚስጥር ለሄኖክ እውቀትን የገለጸለት መልአክ ነው። የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መ.ሄኖክ 28፥13
✔️በብርሃናት ሁሉ ሊቀ ብርሃናት ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ዑራኤል ነው።
✔️ቅዱስ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ ስለሆነ እርሱም መባርቅትን ለጥጋብና ለበረከት እንዲሁም ነጎድጓድን ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መ.ሄኖክ ፮፥፪
➕ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል።
✥ቅዱስ ዑራኤል ልቡናን የሚያበራ እውቀትን የሚገልጽ ርሑሩህ መልአክ ነው። ቅዱስ ዑራኤል ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋአ ልቡናን አጠጥቶት ሰማያዊ ሚስጥራትን ገልፆለታል። ነብዩ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን መጻሕፍት ደርሷል። በሰዓታቱም "ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል፡፡" "ነይ ወደ እኛ ድንግል ሆይ ከእስራኤል ነብያት ከኤልያስና ከኤልሳ እንዲሁም ዑራኤል ጽዋ ልቡናን ካጠጣው ከእዝራ ሱቱኤል ጋር።"
✥ሌላኛው ቅዱስ ዑራኤል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጸ መስቀል ላይ በቀራንዮ በአምስቱ
ቅንዋት (ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ) ሲቸነከር ይህ ብርሃናዊ መልአክ ነው ከጎኑ የክርስቶስን ደም በጽዋ ቀድቶ በዓለም ሁሉ የረጨው።
✥እመቤታችን ወደ ግብፅ በተሰደደች ጊዜ በዚህ የጭንቅ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እየተራዳ መንገድን እየመራት በብርሃን ወደ ሀገረ ግብፅ ቀጥሎም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ወደ ሆነቻት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራት መጥቷል። ማቴ 2÷13-15
✥ሌላው የእውቀትን ብርሃን የገለጸላቸው የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ለሊቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው። እኚም አባታችን በመልአኩ ተራዳኢነት ብዙ ድርሰቶችን ደርሰዋል። እመቤታችንም በምልጃዋ ቅዱስ ዑራኤል የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ዘንድ አድርጋለች። አባ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ይወዷት ስለነበረ አርጋኖን ሌሎችንም ደርሰዋል።
የሊቀ ብርሃናት ቅዱስ ዑራኤል በረከት ተራዳኢነት አይለየን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏