Dr.selemon nutritionist and nursing care services: post #495 — TG.ME

ከምግብ በኋላ ፈፅሞ የማይመከሩ ነገሮች

1. ሻይ አይጠጡ
ሻይ በሰውነታችን ከፍተኛ መጠን ያለው አሲድ  እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ አሲድም በተመገብነው ምግብ ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች እንዲጠነክሩ አልፈጭ እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡

2. አያጭሱ
ምግብ ከተመገቡ በኋላ ወዲያው ሲጋራ ማጨስ አደገኛ ነው ከምግብ በኋላ የሚያጨሱ ሰዎች በሣንባ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነወ፡፡  

             3.    ፍራፍሬ አይመገቡ                                                                                                ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ፍራፍሬ መመገብ አንጀታችን ወዲያውኑ በአየር እንዲወጣጠር ያደርገዋል፡፡ፍራፍሬ መብላት  ከፈለጉ፤ምግብ ከመመግብዎ ከአንድ ሰአት በፊት ወይም ከተመገብዎ ከአንድ ሰአት ተኩል በኋላ ቢሆን ይመረጣል፡፡

       4.  ገላዎን አይታጠቡ                                                                                                 ምግብ ከተመገቡ በኋላ ወዲያውኑ ገላን መታጠብ  በእግርና በጃችን አካባቢ የደም ፍሰት (ዝውውር) መጠኑ እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን በሆዳችን ያለው አካባቢ የደም ፍሰት ይቀንሰዋል፡፡በዚም ምክንያት የምግብ ስልቀጣ ይዳከማል፡፡

      5.  ቀዝቃዛ ውሃ አይጠጡ                                                                                                 ከምግብ በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ከበላነው ምግብ ውሰጥ የሚገኙት ዘይት ነክ ነገሮች ወደ ጠጣርነት ይቀየራቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የምግብ መፍጨት ከመጓተቱም በላይ ወደ ጠጣርነት የቀየረውን ዘይት እና ቅባት ጨጓራ ውስጥ የሚገኝ አሲድ ጋር በማገናኘት በፍጥነት ተሰባብሮ ወደ አንጀት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡ይህም ወደ ስብነት ተቀይሮ  ለካንሰር ሰበብ መጋለጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ከምግብ በኋላ ቀዝቃዛ ውሃ ከመጠጣት ይቆጠቡ፡፡ በምትኩ ለብ ያለ ውኃ መጠጣት የምግብ ልመት ስርአጡ የተሳካ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

6.የእግር ጉዞ አያድርጉ                                                                                                 ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ  የእግር ጉውዞ ማድረግ የምግብ ስልጠቃ ሂደት  በአግባቡ እንዳይከናወን ያደርገዋል፡፡

7. ወዲያውኑ አይተኙ                                                                                                   በልተን ወዲያውኑ ከተኛን የተመገብነው ምግብ በአግባቡ አይፈጭም፡፡ ይህ ደግሞ ለጨጓራ ህመምን ለአንጀት ቁስለት ይዳርጋል፡፡

ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን

ምንጭ:- ጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄና መልስ General Knowledge
❤4
April 20, 2026 169 1