Dr.selemon nutritionist and nursing care services: post #511 — TG.ME

😘❤️ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት (ሴክስ) አለማድረግ በሰውነታችን ላይ ምን ያመጣል? | What Happens When You Stop Having SEX? 💋
✦────────────────────────✦

ብዙ ሰዎች በሥራ ብዛት፣ በውጥረት (stress)፣ በሕመም፣ በግንኙነት መለዋወጥ (መቋረጥ)፣ በግል ምርጫ፣ ወይም በተለያዩ የሕይወት አጋጣሚዎች ምክንያት፤ ለተወሰነ ጊዜ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ሳያደርጉ ወይም ወሲብ ሳይፈጽሙ ሊቆዩ ይችላሉ።

ለሁሉም ሰው የሚሆን አንድ ወጥ የሆነ "ትክክለኛ" የሴክስ መጠን ባይኖርም፤ ጥናቶች እንደሚያሳዩት መደበኛ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ በርካታ አካላዊ እና አእምሯዊ የጤና ጥቅሞች አሉት።

በመሆኑም ለረጅም ጊዜ የግብረ-ስጋ ግንኙነት ወይም ወሲብ አለማድረግ ሊያስከትላቸው የሚችላቸው 11 ሊሆኑ የሚችሉ ተጽዕኖዎች እነሆ፦

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

✅⛔️ ወሲብ አለመፈጸም ሊያስከትላቸው የሚችላቸው 11 ተጽዕኖዎች! | 11 Possible Effects of Going Without Sex! 🐬🐳
――――――――――――――――――――――――――

🧠1️⃣ የጭንቀት ስሜት ሊጨምር ይችላል! | You may feel more anxious! 🧠😬
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በሰውነታችን ውስጥ የጭንቀት ሆርሞኖችን የሚቀንስ ሲሆን፤ ደስ የሚል ስሜት የሚፈጥሩትን እንደ “ኦክሲቶሲን” (oxytocin) እና “ኤንዶርፊን” (endorphins) ያሉ ሆርሞኖችን ያመነጫል።

ይህ ደግሞ ስሜትን ለማስተካከልና ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳል።

❤️2️⃣ የልብ ጤና የሚገኘውን ጥቅም ሊያጣ ይችላል! | Your heart may not benefit as much! 😍💕
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አልፎ አልፎ ብቻ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ሰዎች ለልብ ሕመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።

በተጨማሪም መደበኛ/ቋሚ ሴክስ ወይም ግንኙነት ማድረግ እንደ ቀለል ያለ የአካላዊ ብቃት እንቅስቃሴ ይቆጠራል።

🏃3️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎ ሊቀንስ ይችላል! | You may get less physical activity! 🏃
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በሚደረግበት ወቅት ካሎሪ የሚቃጠል ሲሆን፤ የልብ ምትም ይጨምራል።

ይህ ደግሞ በአጠቃላይ ለዕለታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል።

🧩4️⃣ የማስታወስ ችሎታ ያን ያህል መነቃቃት ላይኖረው ይችላል! | Memory may not get the same boost! 🧩
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አንዳንድ ምርምሮች እንደሚያሳዩት መደበኛ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ፤ በተለይም በዕድሜ በገፉ አዋቂዎች ላይ የተሻለ የማስታወስ ችሎታና የአእምሮ ንቁነት (cognitive function) እንዲኖር ያደርጋል።

🛡5️⃣ የበሽታ መከላከል አቅም ሊቀንስ ይችላል! | Your immune system may be less active! 🛡
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

መጠነኛ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ፤ ሰውነታችን በሽታዎችን ወይም ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚረዳውን "ኢሚዩኖግሎቡሊን ኤ" (IgA) የተባለ በሽታ ተከላካይ አንቲቦዲ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።

ስለዚህ ወሲብ መፈፀም ማቆም በሽታ የመከላከል አቅማችንን ሊቀንሰው ይችላል።

💑6️⃣ በትዳር ወይም በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያለው መቀራረብ ሊቀንስ ይችላል! | Your relationship may feel less connected! 💑
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ለብዙ ጥንዶች የቅርብ አካላዊ ግንኙነት (መቀራረብ) (intimacy) ስሜታዊ ትስስርን፣ መግባባትን፣ መተማመንን፣ እና በትዳር ሕይወት ላይ እርካታ እንዲኖር ያደርጋል።

👨7️⃣ የወንዶች የፕሮስቴት ጤና ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል! | Men's prostate health may be affected! 👨🤦‍♂️
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በተደጋጋሚ የዘር ህዋስ ፈሳሽ (ስፐርም) መልቀቅ ወይም ማፍሰስ (ejaculation) ለፕሮስቴት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

ሆኖም ግን ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ ማድረግ ወሳኝ ቢሆንም፤ የፕሮስቴት ጤና በብዙ ሌሎች ነገሮችም ይወሰናል።

😴8️⃣ የእንቅልፍ ጥራት ሊቀንስ ይችላል! | You may sleep less soundly! 🛌💤
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማጠናቀቂያ (እርካታ) (orgasm) ወቅት የሚለቀቁት እንደ "ኦክሲቶሲን" እና "ፕላላክቲን" (prolactin) ያሉ ሆርሞኖች፤ ሰውነት እንዲዝናና (ዘና እንዲል) እና ጥልቅ እንቅልፍ እንዲወስደን ይረዳሉ።

💆9️⃣ የዕለት ተዕለት የሰውነት ሕመሞች ሊባባሱ ይችላሉ! | Everyday aches and pains may feel worse! 💆
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በሴክስ ወቅት የሚመነጩት 'ኤንዶርፊኖች' እንደ ራስ ምታት፣ የወር አበባ ህመም፣ የመገጣጠሚያ ህመም (አርትራይተስ) (arthritis)፣ እና ሌሎች ጥቃቅን ቁስለቶችን ለመቀነስ ይረዳሉ።

🌸🔟 የመራቢያ አካላት (የብልት) ተግባር በጊዜ ሂደት ሊለወጥ ይችላል! | Sexual function may change over time! 🌸
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የማረጥ ዕድሜ ላይ ለደረሱ ሴቶች፤ መደበኛ የሴክስ ግንኙነት ማድረግ የብልት ግድግዳዎች እንዳይሳሱ (tissue elasticity) እና የእርጥበት መጠንን ለመጠበቅ ይረዳል።

በወንዶች ላይ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የግብረ-ስጋ ግንኙነት አለማድረግ ከብልት አለመቆም ችግር (erectile dysfunction) ጋር ሊያያዝ እንደሚችል አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ።

🩺1️⃣1️⃣ የደም ግፊት ሊጨምር ይችላል! | Blood pressure may rise! 🚑
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

መደበኛ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ውጥረትን
ስለሚቀንስና የደም ዝውውርን ስለሚያሳልጥ የደም ዝውውርን ለማስተካከል ይረዳል።

የግብረ-ስጋ ግንኙነት በማያደርጉበት ጊዜ የደም ግፊት የመጨመር ዕድል ይኖረዋል።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

✅💡 ዋናው ነጥብ! | The Bottom Line! 🪧
――――――――――――――――――――

የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የአጠቃላይ ጤናችን አንዱ አካል ብቻ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች የግብረ-ስጋ ግንኙነት ባታደርጉም እንኳ፤ ይህ ማለት “ጤናማ አይደላችሁም” ማለት አይደለም።
July 9, 2026 68