የኔ ልጅ ...ልጄ .....ከተመሰጥኩበት የሀሳብ ባህር ያባነነኝ ቀዝቃዛ የተረጋጋ የአዛውንት ድምፅ ነው።… — ኢትዮ 𝐖𝐢𝐬𝐝𝐨𝐦 𝐋𝐢𝐛𝐫𝐚𝐫𝐲 — TG.ME

የኔ ልጅ ...ልጄ .....ከተመሰጥኩበት የሀሳብ ባህር ያባነነኝ ቀዝቃዛ የተረጋጋ የአዛውንት ድምፅ ነው። አአአ"ቤት አባቴ ምን ልርዳዎት የበፊቱን መዘግየት አሁን በመፍጠን ላካክሰው ሳይሆን አይቀርም....በጥድፊያ ጠየዃቸው በዚች ስልክ ለልጄ ደውይልኝ...."ማ የያዟትን ትንሽዬ ጠቅጠቅ ስልክ እያቀበሉኝ....ቆይ ላስታውስ ....ብለው አፋቸውን ጠረጉ....የምነግርሽን ፃፊ...09...እእ..43...ቀጣዩ....እንደምንም ብለው ቁጥሩን ነገሩኝ ....ራሴን ታዘብኩት ከራሴ ወጪ የሁለት ሰው ስልክ እንኳን በቃሌ አልያዝኩም ሳፋሪ ኮም ሲሜን እንኳን አላውቀውም እሳቸው ግን.... በዚ መገረም ውስጥ እንዳለሁ አውርተው ጨርሰው ሌላም ስልክ ሰተውኝ ደወልኩላቸው......ስልክ ሲያወሩም እንዲ ስሜታዊ መሆን ይቻላል ለካ....ልጆቻቸውን የሚያወሩበት ድምፅ እርጅና ያልገደበው የፍቅር የናፍቆት የጉጉት የደስታና ሀዘን ቅልቅል ድምፀት አለው.... የልጆቻቸው.... የልጅ ልጆቻቸውን ጤና ደንነታቸውን ደጋግመው ይጠይቃሉ። ለይምሰል ሳይሆን የእውነት ደና መሆናቸውን ለማወቅ....በወሬቸው... መሀል....ቸሩ መድሀኒያለም ምን አጉድሎብኝ ክብሩ ይስፋ ደናነኝ... ጉልበቴን ነው ትንሽ ስራመድ የሚይዘኝ ይሻለኛል...ይላሉ....ሰውነታቸው እንጂ ተስፋቸው አላረጀም። የእውነት ቀናሁ....መኖር አያደክምም እንዴ አልኩ ለራሴ...? ነውስ ከአዲስ እድሜ ጋር አዲስ ብርታት አብሮ ይሰጠናል....? "ስልካቸውን በብዙ ምርቃት አሳርገው ጨረሱ....ምርቃቱ ወደ እኔ ዞሮ....ለትንሽ ነገር Thank you...ማለት የፈረንጆች ድንቅ ባህል ይመስለኝ ነበር። ለካስ ከአንገት በላይ ሳይሆን ከልብ በፈለቀ ከምስጋናም በላይ በሆነ ምርቃት ልብን ማረስረስ የሀበሻም ባህል ነው....አስባሉኝ...ምን አድርጌ ነው ይሄ ሁሉ ምርቃት እስክል ድረስ....ዛሬ እመቤታችን ናት ባንቺ ተመስላ የልጆቼን ድምፅ ያሰማችኝ...ተባረኪ....የመረቁኝን ልፃፍ ብል እራሱ ሁሉንም አላስታውሰውም በዛላይ ስፅፍ ማደሬ ነው። ግን ልቤን የነካው ነገር እመቤታችን ባንቺ ተመስላ ሲሉኝ ነው ውስጤ ሽምቅቅ አለ ግን እምነታቸው አስደነቀኝ በኔ በተራዋ ሴት የአምላክ እናት ካዩ ሰውነትን ምን ያህል ቢያከብሩት ነው...?! የልጆቻቸውን ድምፅ ስለሰሙ ብቻ ለእመቤታችን ምስጋናን ያቀርባሉ። ተቀብለው ዘወር አይሉም ስልኩ ተዘግቶም ምስጋናቸው አልቆመም....እኛስ ማን ቢደውልል ለማን ብንደውል ነው ማመስገኛ ሰበብ የምናገኘው...? የልጆቻቸውን ድምፅ አልናቁትም....እኔም እንደሳቸው በሆንኩ አልኩ አንሰው የታዩኝ ነገር በጎሉልኝ... ማመስገኛ ምክንያቴ በሆኑ.... ተሰናብተው መርቀውኝ ከሄዱ በኋላ ሮጬ ተከተልካቸው.... አባባ ....ድምፄን ሰምተው ዘወር አሉ ፈገግታቸው የብዙ አመት ትውውቅ ያለን ያህል እንዲሰማኝ አደረገኝ። አይ ሰው ፈገግታ ያሸንፈዋል ለካ በቃ በአንድ ጊዜ ፍርሀት ትቶኝ ሲሄድ ታወቀኝ...መንገዳችን አንድ ላይ ነው አብሬዎት ልሂድ.... እጥፍ ድርብ ፈገግታ ...ቸሩኝ አብረን መሄድ ጀመርን...ሰው ቶሎ አልግባባም...ካልተግባባው ደግሞ አላወራም እሳቸው ግን የመተዋወቅ ስሜትን በልቤ ስላሳደሩ...ማውራቱን ተያያዝነው ስላሳለፍት...ስላለፉበት...ስላሳለፋቸው...በአጭሩ ተረኩልኝ። ለካ ሽበት ቀለም እንደመቀባት ቀላል ፈጣን እርምጃ አይደለም ....ወይም ፀጉር እንደመቆረጥ እንደ ማሳደግ የአመት ወይም የወሮች...የቀኖች የደቂቃ እድሜ ብቻ አይጠይቅም። ሽበት ለማብቀል...ባለ ሺውበት ለመሆን መታደል ብዙ መኖርን ይጠይቃል። ብዙ የኖረ ደግሞ ወደደም ጠላም ብዙ ያውቃል።...የተጨማደዱ ፊቶች ለካ ብዙ አይተዋል...የጎበጡ ትከሻዎች ለካ ብዙ ተሸክመዋል... በስተመጨረሻ አንድ ጥያቄ አቀረብኩላቸው...ካሳለፉት ህይወት የተማሩት ትልቁ እና ዋነኛው ነገር። ብዙ ያስባሉ ብዬ ገምቼ ነበር እሳቸው ግን ፈርጠም ባለ ድምፅ በከዘራቸው መሬቱን ጥብቅ አድርገው ይዘው.....አለመፍረድ...አሉኝ። የኔ ልጅ እኔ ሽማንሌ ነኝ...በእድሜዬ በጎም ክፉም አይቻለሁ። ግን አብዛኛው በሚባል ደረጃ የህይወት ፈተናዎቼ የመጡት ፍርዱን ለአምላክ ባልተውኳቸው ነገሮች ናቸው። የወጣትነት ዘመን ደግሞ ትችያለሽ...ጠንካራ ነሽ ብዙ ብዙ ይልሻል....ያኔ የወደቁ ሰዎች...ወይም ያልተሳካላቸው ሰዎች ላይ መፍረድ ይቀናሻል። እኔም እንደዛ ነበርኩኝ። መፍረድ ይቀናኛል። ሰው ለምን ይበደራል..ስራ አይሰራም እንዴ ብሩን አይቆጥብም ብዬ ተበድሮ ባልከፈለ ሰው መፍረዴ ስህተት መሆኑ የገባኝ። አጣብቂኝ ውስጥ ገብቼ ደሞዜ አልበቃኝ ብሎ ተበድሬ መክፈል ሲያቅጠኝ ነው። ፍቅር ጅልነት ነው። የምን አፍቅሮ መጃጃል ያለው አንደበቴ መሳሳቱን ያወኩት አፍቅሬ ..  እኔም እንዳልኳቸው አፍቃሪዎች ስሆን ነው። ለምን ያቀብጡታል ጥፋቱ የነሱ ነው ....ምነው የኔ ልጅ በሆነ ጨምላቃ...ልክ አስገባው ነበር..ብዬ የፈረድኩባቸው ወላጆችን የተረዳኋቸው እንደነሱ አይነት ልጅ ወልጄ ....ልጅ በቅጣት እንደማይስተካከል ሲገባኝ ነው። አየሽ የኔ ልጅ በምታይው በምትሰሚው በየኛውም ነገር አትፍረጂ። በማያገባሽ ገብተሽ ስትፈርጂ ፈጣሪ ደግሞ በነዛ ሰዎች ችግር ውስጥ አንቺንም ያስገባሻል ያኔ በመፍረድሽ ትፀፀቺያለሽ። የኔን እድሜ አንቺ ሩብንም አልኖርሽውም እና ልጄ.....የተቀረውን እድሜ በሰላም በደስታ እና ካለ አስፈላጊ ስቃይ እድትድኚ አትፍረጂ እሺ አሉኝ....!!! እሺ አባባ አልኳቸው....!!! ✍🏽#wisdom_library1 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━ 👇👇JOIN AND SHARE👇👇 @wisdom_library1

August 4, 2026 50