አለም ላይ ያሉት ውቅያኖሶች በእየለቱ ከሚያናውጣቸው ማዕበል ባልተናነሰ የሰው ልጆች ልብ ውስጥም ታላቅ ማዕበል… — ኢትዮ 𝐖𝐢𝐬𝐝𝐨𝐦 𝐋𝐢𝐛𝐫𝐚𝐫𝐲 — TG.ME

አለም ላይ ያሉት ውቅያኖሶች በእየለቱ ከሚያናውጣቸው ማዕበል ባልተናነሰ የሰው ልጆች ልብ ውስጥም ታላቅ ማዕበል ይነሳል። ታላቅ ማዕበል የበረታ አውሎ ንፋስ የሰውን ልብን ክፍኛ ያውከዋል። ወጀብ በበረታ ቁጥር ሰው በራሱ ልብ እራሱ ይሰምጣል ረግቶ መቆምም ሆነ ተረጋግቶ ማሰብ ያቅተዋል። ከልብ የተነሳው ወጀብ መላ አካሉን በፍርሀት ይሸብበዋል። ዛሬኑ እንዲጠራጠር እና ነገውን እንዲፈራ ያደርገዋል። ነገር ግን....ከማዕበል በላይ "ካለ"ማዕበል መኖር ውቅያኖሶች ህይወት አልባ ያደርጋቸዋል። ባህርም ሆነ ውቅያኖስ ሳይንቀሳቀስ ረግቶ በቆየ ቁጥር የያዘው ውሀ እየሸተተ እና እየተበላሸ ይሄዳል። በዛ ውስጥ የሚኖሩትም ነፍሳት ይሞታሉ። ማዕበል ሲመጣ ግን ያንን የረጋ ውሀ ይበጠብጠዋል ከውጪ ሁኖ ለሚያየው ቢያስፈራም በውስጡ ለሚኖሩ ፍጥረቶች ግን እጅግ ጠቃሚ ነው። መናወጡ ህይወትን ይቀጥላል።...አደፍርሶ ያጠራል። በህይታችንም ልክ እንደዚ ነው። ማዕበል ተነስቶ ሲያናውጠን  ብንፈራም ብንርበተበትም ከማዕበሉ ለማምለጥ ትግል እናደርጋለን። ያ ትግል ደግሞ ጠንካሮች ያደርገናል። ህይወታችን እንዲቀየር ትልቅ ተፅዕኖ አለው። ✍🏽#wisdom_library1 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━ 👇👇JOIN AND SHARE👇👇 @wisdom_library1

July 31, 2026 20