መቼም ቢሆን የእውነት ፍቅር እንዳይዝህ እሺ...! እውነት ትጎዳለህ....እስካሁን ስላላፈቀርክ እድለኛ ነህ....ከየቷም ሴት የእውነት ፍቅር እንዳይዝህ.... የኔ መልስ የለበጣ እሺ ነበር....ጎደኞቼ አብዛኛዎቹ ቱ...ፍቅር ያሉ የከተማ መናኒያን ናቸው የእውነት ከማፍቀር ኮብልለው የማስመሰል ፍቅር ላይ የተጣበቁ... የፍቅር በረከቱም እርግማኑም አንቺ መተሽ የወንድነቴን እስክፈተን ደና ነበርኩ። በአረጋሀኝ ዘፈን መረጋጋቴን አጥቼ ኸረ እኔማ አዘንኩኝ በራሴው ተፈጥሮ...." ባላወኩሽ ኖሮ.... ብዬ የተዋወቅንበትን ቀን በሳምንት ስምንት ቀን እስክረግመው ድረስ....ደና ነበርኩ...!!! አደራ ፍቅር እንዳይዝህ ሲሉኝ....ፍቅርን ባልፈራውም አልተዳፈርኩትም ነበር። ፍቅር ለካ የአባሮሽ ጨዋታ አይደለም አሯሩጦ አይዝም...!! አዘናግቶ ነው የሚይዘው ...."ተይዣለሁ.." ፍቅር መያዝ ነው.... ያውም በስሜት በቀልብ መያዝ ....መያዝ ደግሞ ከሰው ቁጥጥር ዉጪ ነው። የመጀመሪያ ያየሁሽ ቀን ደስ አልሽኝ እንጂ ልቤ በጭሬሽ ለፍቅር አላሰበሽም....ራስሽ ነበር የተዋወቅሽኝ። ልክ እንደ እፉዬገላ ነበርሽ ......ደስ የምት ተንሳፋፊ በራሪ.... መብረረሽ የማይረብሽ....አምነው የሚከተሉሽ አይነት....ሴት ነበርሽ...! እፉዬ ገላ ቢጨምቋት ትጠፋ ትሞት ይሆናል እንጂ ሰውን ምን አድርጋ ልትጎዳ ልክ እንዳንቺ..... የኔ ለስላሳ ....ይዤሽ ነበር እኮ ግን እፍ አልኩሽ ያው ነፃነት እንድታገኚ...ግን እያየሁሽ ከኔ መራቅ ጀመርሽ...እየሳኩ ተከተልኩሽ....ለካ ውሀ ብቻ አይደለም አንቺም ስትወስጂ እያሳሳቅሽ ነው...!! ተከተልኩሽ....ግን ድጋሚ ልይዝሽ አልቻልኩም ከማላውቀው ከማልደርስበት ከማላወጣሽ ሌላ አለም ውስጥ ገባሽ...ብቻዬን ተመለስኩኝ። ፍቅር እንዳይዝህ ያሉኝ ጎደኞቼን አገኘኋቸው...ብለንህ ነበር አሉ....እሰይ ምክር አልሰማ ስትል አሉኝ። በፍቅር ያዘነ በምን የደሰታል...? ቢያፅኑኝ እንኳን የማይፅናና ደስታ የራቀው ልቤን የባሰ አደሙት ...ተውኳቸው። ፍቅር ካንቺ ያዘኝ ብዬው የያዘኝ....? ማፍቀር ፈልጌ ነው ያፈቀርኩሽ...አይደልም። ማፍቀር በጣም ያስፈራኝ ነበር። ማለት ዝግጁ ስላልሆንኩ.....የፍቅር በረከትንም እርግማንንም መሸከም የሚችል ትከሻ እንደለለኝ አውቅ ነበር። ግን መተሽ ተዋወቅሽኝ....ሳላውቅ ያለ ገዛ ፍቃዴ ወደድኩሽ... ማፍቀር በምርጫ እና በጊዜ ቢሆን አንቺን ነው ደግሜ የማፈቅረው ግን ጊዜው አሁን አይደለም። ያለ ጊዜው የመጣ በጊዜው ከመጣ ምጥ በላይ በጣም ያስጨንቃል። እና እኔም ይሄኛውን ምጥ ፈልጌው አላውቅም ግን በቃ አፈቀርኩሽ...ምን ላድርግ....?! ማድረግ የነበረብኝ ከረፈደ የገባኝ ነገር ያኔ ስንተዋወቅ ፊት ብነሳሽ አሪፍ ነበር ባንግባባ ባልከተልሽ ጥሩ ነበር.... ነበር....!!!! ✍🏽#wisdom_library1 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━ 👇👇JOIN AND SHARE👇👇 @wisdom_library1
መቼም ቢሆን የእውነት ፍቅር እንዳይዝህ እሺ...! እውነት ትጎዳለህ....እስካሁን ስላላፈቀርክ እድለኛ… — ኢትዮ 𝐖𝐢𝐬𝐝𝐨𝐦 𝐋𝐢𝐛𝐫𝐚𝐫𝐲 — TG.ME
July 30, 2026 18