Billionaire Mindset️: post #1398 — TG.ME

ልቆ የመገኛው ምስጢር!

በዚህ ውድድርና ፉክክር በሞላበት አለም ውስጥ ስንኖር ልቆ ከመገኘት ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ የለንም፡፡ በተሰማራንበት መስክም ሆነ በስብእናችን ልቀን ካልተገኘን ፈጠነም ዘገየም መጨረሻ ላይ መገኘታችን የማይቀር ነው፡፡ ልቆ የመገኛው መንገድ ደግሞ ለፍጽምና መስራት ነው፡፡

በባህሪይም ሆነ በማንኛውም የስራ ዘርፍ ውስጥ ፍጹም ሆኖ መገኘት በፍጹም የማይቻል ነገር ነው፡፡ ሆኖም፣ ለፍጽምና መስራት እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ምንም እንኳን ፍጽምና ላይ ባንደርስም ልህቀት ደረጃ ላይ መድረሳችን አይቀርምና፡፡
መጠንቀቅ የሚገቡን ነገሮች፡-

• ፍጹም መሆን አይቻልም በሚል ሰበብ መለወጥና ማሳደግ የምንችላቸውን ነገሮች ችላ ማለት፡፡

• እኛ ፍጹም ሳንሆን ከሌላው ሰው ምንም ስህተት እንዳይገኝበት መጠበቅ፡፡

• ፍጹም ለመሆን የሚሰሩ ሰዎችን ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮችን መናገር፡፡

ዝም ብላችሁ ፍጽምናን ተከታተሉት፡፡ አንድ ቀን ልህቀት ላይ መድረሳችሁ አይቀርም፡፡

       መልካም ቀን!
🔥4
August 18, 2026 302