Billionaire Mindset️: post #1393 — TG.ME

የማንኛውም ቢዝነስ 5 ወሳኝ ምሶሶዎች! 🏢📊

የጀበና ቡና መሸጫ ይሁን ወይም ትልቅ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ፤ ማንኛውም ቢዝነስ በስኬት እንዲቀጥል እነዚህ 5 ምሰሶዎች ሊኖሩት ግድ ይላል ።

እሴት መፍጠር (Creation)፦ የንግድ ስራ መጀመሪያ ለሰዎች ችግር የሚፈታ፣ ሰዎች ገንዘብ ሊከፍሉለት ፈቃደኛ የሆኑትን ምርት ወይም አገልግሎት ማዘጋጀት ነው። ይህ ምርት ወይም ግልጋሎት ከሌሎች በገበያው ውስጥ ካሉት የተሻለ የውድድር ብልጫ (Competitive Advantage) ሊኖረው ይገባል። ብዙዎች በንግድ ውስጥ ራሳቸው ያስፈልጋል ብለው ያሰቡትን ወይም ከበቂ በላይ አቅርቦት ያለውን ምርት ለገበያ በማቅረብ ለኪሳራ ይዳረጋሉ ።

ማርኬቲንግ (Marketing)፦ ደምበኛ ያላወቀው ምርት የጨለማ ውስጥ ጥቅሻ ነው! ምርት ወይም አገልግሎትን ለታለመው ደንበኛ (Target Audience) ማሳወቅና ማስተዋወቅ በንግድ አለም ውስጥ ሌላው ወሳኝ ተግባር ነው። ሰዎች አንድን ምርት ካላወቁት፣ ቢፈልጉት እንኳ ለገዙት አይችሉም ። የምርቱ ባለቤትም አትራፊ ሆኖ ገበያው ውስጥ መቆየት አይችልም።

ሽያጭ (Sales)፦ ምርትን ማስተዋወቅ ሰዎችን ሲስብ፣ ሽያጭ ደግሞ ደምበኛን አሳምኖ፣ ጥያቄዎቻቸውን በአግባቡ መልሶ ምርቱን ወደ ገንዘብ የመቀየር ሂደት ነው። የአንድን ንግድ ህልውና ከሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ ትልቁ የገንዘብ ፍሰት ነው። ገንዘብ የአንድ ድርጅት ደም ነው።

እሴቱን ማድረስ (Value Delivery)፦ የተተዋወቀውና የተሸጠው ምርት ወይም ግልጋሎት የደምበኛውን ፍላጎት ማርካት ይኖርበታል። ለደንበኛ የተገባለት ቃል በታማኝነትና በጥራት ከደረሰው.መልሶ መላልሶ ይመጣል። ብዙ ግዜ ተመልሶ ሲመጣ ብቻውን ሳይሆን ተመሳሳይ መፍትሄ የሚፈልጉ ሰዎችን በማምጣት የማይከፈለው የምርታችን አስተዋዋቂም ሊሆን ይችላል።

ፋይናንስ (Finance)፦ በመጨረሻም የአንድ የንግድ ድርጅት ትልቁ አላማ ለባለቤቶቹ ትርፍ ማስገኘት ነው። ስለዚህ የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ሁሉ በአጠቃላይ ገቢው ከወጪው በልጦና አትርፎ  የንግዱን አስተማማኝነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይህን ለማድረግ የገንዘብ እንቅስቃሴውን ስርአት ባለው መንገድ መከታተል ያስፈልጋል። የገንዘብ ስርአት የሌለው ንግድ፣ ኮምፓስ ይሌለው መርከብ ነው፣ ሁለቱም መሳሳታቸውን የሚያውቁት ከከሰሩ በኋላ ነው።

ብዙ ጀማሪዎች ንግድ ማለት የንግድ ፈቃድ ማውጣት ብቻ አድርገው ይቆጥሩታል። በዙዎቹ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ከጨዋታ ሆነው የሚዘጉት ከላይ ካየናቸውን መሰረታዊ የንግድ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ስለሚያጎድሉ ነው ። የእርስዎ ቢዝነስ ከአምስቱ የትኛው ምሶሶ ላይ ደካማ ነው? ያወቁትን ክፍተት ደግሞ ዛሬውኑ ያስተካክሉ!

@winnersecret
❤3
June 24, 2026 1.1K 15