📢 ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ለመቀላቀል የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦
ዩኒቨርሲቲው በኢንጂነሪንግ፣ በጤና እና በቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጆቹ በ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በዚህ መሠረት፣ በቀድሞ ማስታወቂያ መሠረት የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በአካል በመገኘት ከዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የምዝገባ ኃላፊዎች ጋር በተዘጋጁ የመሰባሰቢያ ቦታዎች ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
👉 ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የምዝገባ ጊዜና ቦታ
ጊዜ፡ ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም
ቦታ፡ ሆሳዕና ከተማ - ሃዲያ ባህል አዳራሽ የምዝገባ ጣቢያ
👉ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
*ከ8ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች (ኦርጅናል)
*4 ፓስፖርት መጠን ፎቶ
*ክሊራንስ
*ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ
👉ተጨማሪ መረጃ እና በየምዝገባ ጣቢያው የተመደቡ ኃላፊዎችን ስልክ ለማግኘት (https://www.etdu.edu.et/Notice)
📢 ማሳሰቢያ
ተማሪዎች አሁን እየተማሩ ባሉበት ቅርብ የምዝገባ ጣቢያ በመገኘት ብቻ መመዝገብ እንደሚችሉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!
📌 Telegram channel https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website http://www.etdu.edu.et
📌Facebook https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok https://www.tiktok.com/@ethiopiandefenceuniversi
www.etdu.edu.et
Ethiopian Defence University - News Portal
Stay updated with the latest news and announcements from Ethiopian Defence University
25
10June 15, 2026 11.6K 5