#የውጤት_ዜና_ለወልቂጤ_ከተማ_አስተዳደር
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
ወሄም ሳረናሁም ! ወሄም እማትሜ ሳረንደም!
የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን በፌዴራል ደረጃ የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል
#ወልቂጤ| ሰኔ 15/2018 ዓ.ም
ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ባዘመኑ ከተሞች ምድብ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት አገልግሎት አፈፃፀም ምዘና 85.66% ውጤት በማስመዝገብ በምድቡ 2ኛ ደረጃ በማግኘቱ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል።
ከተማ አስተዳደሩ ተቋሙን በልዩ ትኩረት በመከታተልና በመደገፍ ፤ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥንን በማዘመን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የመስራት ወጤት ነው።
ለዚህ ውጤት መመዝገብ አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ አመራሮችና ማህበረሰብ ባለድርሻ አካላትና አጠቃላይ የተቋም ባለሞያዎች ምስጋና ይገባችኋል።













