⛪️ የእርዳታ ጥሪ ⛪️
👉🏾 የዓባይ ቅድስት አርሴማ ገዳም መነኮሳት ይጣራሉ!
በጾመ ፍልሰታ ልንረባረብበት የሚገባ የበረከት ጥሪ
👉 ከጾም ቁርሳችን ላይ ጨመርመር አድርገን ለገዳማዊያን አለንላችሁ እንበላቸው
የገዳሙ መነኮሳት እንዲህ ይሏችኋል
ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ቦረና ወረዳ በምትገኘው በዓባይ ገዳመ አስቄጥስ አቡነ አረጋዊ ወቅድስት አርሴማ ወቅዱስ ቂርቆስ ገዳማችን ላይ በደረሰብን የድሮን ጥቃት 2 መነኮሳይያት እናቶቻችን በሞት ከማኅበራችን ሲለዩብን ከ14 በላይ ደግሞ ቁስለኛ ሆነውብናል።
በአጠቃላይ በደረሰብን የድሮን ጥቃት
👉 የመናንያኑ ሙሉ የዓመት ቀለብ ወድሞብናል።
👉 ቤተ እግዚአብሔሩ (የእህል ማከማቻ ማዘጋጃና መመገቢያ ቤት) ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎብናል።
👉ከዓባይ ወንዝ የተጠለፈ የልማት የውሃ መስመሩ ተመትቶብን የቀረነው መነኮሳት ልማት አቁመናል።
👉በገዳሙ ውስጥ የምንጠቀምቀት የውሃ ታንከር ተሰብሮብናል ።
👉የገዳማችን ሙሉ የማዕድ ቤት ማቴሪያል ተቃጥሏል።
👉 ወጣትና አምራች መነኮሳይያት በጥቃቱ የአልጋ ቁራኛ ሆነውብናል።
ሌሎቻችን ቀሪ መነኮሳት ደግሞ የተጎዱትን አስታማሚና ተንከባካቢ በመሆናችን በገዳሙ ውስጥ የነበሩ ልማቶቻችን ሙሉ በሙሉ ቆመውብናል።
ስለዚህ እናንተ በዓለም ያላችሁ የሰማዕቷ ወዳጆች እርዱን ደግፉንና ገዳማችንን ወደ ነበረበት ቁመናው እንመልሰው።
በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል
እኛም ልጆቻቸው አይዟችሁ አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል።
በግዮን ዓባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅ/አርሴማ አቡነ አረጋዊ ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም የባንክ ቁጥሮች
ንግድ ባንክ 1000786890008
አባይባንክ 2531113205827016
አቢሲንያ ባንክ 273010203