ራስህ ስማ!
🪢💥🪢💥
ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ወደ ሃኪም ዘንድ ሄዶ "ዶክተር እባክህን ባለቤቴ ከርቀት የመስማት ችግር ጀምሯታል ምን ላድርግ" ይለዋል
ዶክተሩም "ከምን ያህል ርቀት መስማት እንደማትችል ታውቃለህ?" ይለዋል ሰውየውም አላውቅም ሲል ይመልሳል ዶክተሩም በል ከምን ያህል ርቀት መስማት እንደማትችል አጣርተህ ና ይለዋል።
ሰውየውም እንደተባለው ወደ ቤቱ ይሄድና ከ 5 ሜትር ርቀት ላይ ቆሞ ሚስቱን "የእኔ ቆንጆ ዛሬ ምሳ ምንድነው ይላታል ዝም መልስ የለም አሁንም 4ሜትር ላይ ሆኖ "የእኔ ቆንጆ ዛሬ ምንድነው ምሳ ይላል" አሁንም ዝም ትለዋለች።
እንዲህ እያደረገ አጠገቧ ድረስ ይቀርብና "የእኔ ቆንጄ ዛሬ ምንድነው ምሳ?" ይላል ሚስትም በንዴት ዞራ "ምን ሆነሃል ዛሬ ቀን? አሁን እኮ ለ5ተኛ ጊዜ ነው ስጠይቀኝ ምስር ወጥ አልኩህ እኮ" አለችው።
👉👉ለካ የማይሰማው እሱ ኖሯል👈👈
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ለሌሎች የምትሰጠውን የፍርድ ሚዛን፣ መጀመሪያ የራስህን ህይወት ለመመዘን ተጠቀምበት። የሰውን ህይወት ለማስተካከል ከመነሳትህ በፊት፣ የራስህ ‘ጆሮ’ በትክክል እየሰራ መሆኑን አረጋግጥ።
አዲሱን ቬነስያ ይቀላቀሉን ፣ ይወዱታል!
https://t.me/veni212121
July 14, 2026 747 2