ተወዳጆች ሆይ… ✨ ​ጸሎት የቃላት ድርድር ወይም ከልማድ ስሜትን/ትኩረትን አደብዝዞ» የምንደግመው ደረቅ… — ተግሳጽ — TG.ME

ተወዳጆች ሆይ…

​ጸሎት የቃላት ድርድር ወይም ከልማድ ስሜትን/ትኩረትን አደብዝዞ» የምንደግመው ደረቅ ንግግር አይደለም፤ የነፍሳችን እውነተኛ ናፍቆትና ከፈጣሪዋ ጋር የምታደርገው ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት እንጂ!

​በዕለት ተዕለት ውካባና በምድራዊ ጭንቀት ውስጥ ስናልፍ ነፍሳችን ትደክማለች፣ ትጠማለችም። ጸሎት ደግሞ ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ክብደትና ውጣ ውረድ በላይ ተስፈንጥረን ወደ መንፈሳዊው ዓለም የምንወጣበት፣ ከዘላለም አምላካችን ጋር ተገናኝተን እውነተኛ ዕረፍትን የምናገኝበት የተቀደሰ ድልድይ ነው።

🕊️ ጸሎት — የደከመች ነፍስ የምትታደስበትና የሚሞላባት የሕይወት ውሃ ነው።

💡 ጸሎት — የወሰን ያለው ፍጡር ወሰን የሌለውን አምላክ የሚያቅፍበት ድንቅ ምስጢር ነው።

🕯️ ጸሎት — ሰው ከምድር አቧራ ተነስቶ ከሰማዩ አባቱ ጋር የሚነጋገርበት ታላቅ ክብር ነው።

​ዛሬም ቢሆን የትም ብንሆን፣ የቱንም ያህል በስራና በምድራዊ ነገር ብንከበብ፣ ነፍሳችን ወደ አባቷ እንድትበር ዕድል እንስጣት።

የጸሎት ጊዜያችንን የሥጋችን ሳይሆን የነፍሳችን እውነተኛ የዕረፍትና የደስታ ሰዓት እናድርገው።

​የአምላካችን ሰላምና ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን! 🙏

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ❣️

✍️ / ዑራኤል



ማንኛውም ሀሳብ
👇👇👇
@Mogesinewokibrene
❤5🙏1
August 24, 2026 760 7