ሰዎችን በእውነት መለወጥ፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ መምራት ወይም ሐሳባችንን እንዲረዱን ማድረግ ከፈለግን በቀጥታ ከአእምሯቸው ይልቅ አስቀድመን ልባቸውን መንካት አለብን።
አንድን ሰው በክርክር ወይም በምክንያት ማሸነፍ አእምሮውን ሊረታው ይችላል፤ ነገር ግን ልቡን ካላሸነፍነው ለውጡ ዘላቂ አይሆንም።
የሰው ልጅ ሁልጊዜ በምክንያት ብቻ ሳይሆን በፍቅር፣ በእርህራሔ፣ በሰላምና በትህትና ይማረካል።
ፍቅርና ርኅራኄ በተሞላበት አቀራረብ የሰውን ልብ ከከፈትን፣ አእምሮው በተፈጥሮው ለበጎ ሐሳብ ክፍት ይሆናል።
የተወደዱት አባታችን አቡነ ሽኖዳ እንዳስተማሩን፦
"የምትነጋገሩትን ሰው አእምሮ ከመንካታችሁ በፊት ልቡን ለመንካት ሞክሩ፤ ልቡን ማሸነፍ ከቻላችሁ አእምሮውንም በእርግጥ እንደምታሸንፉ እርግጠኞች ሁኑ።"
እኛም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን፣ ለሰዎች በምናሳየው መልካም አቀራረብና በእውነተኛ ፍቅር የሰዎችን ልብ እያሸነፍን የበጎነትና የሰላም መንገድ መሪዎች እንሁን!
✍️ / ዑራኤል

