ይህንን ያውቃሉ ⁉️ ረሱል ﷺ ለዚህ ሰሀቢይ ያደረጉት ዱዓ ህይወቱን በሙሉ ረድቶታል፡፡ "ሀብትህን የበረካ… — ከዋክበቶቹ | النجوم | — TG.ME

ይህንን ያውቃሉ ⁉️

ረሱል ﷺ ለዚህ ሰሀቢይ ያደረጉት ዱዓ ህይወቱን በሙሉ ረድቶታል፡፡
"ሀብትህን የበረካ ያድርግልህ"  የሚል ነበር ሀብቱ የበረካ ሆነ ከሰሀባዎች ውስጥ ሀብታሙ ሰሀባ ነበር፡፡

በመዲና በነበረው ንግዱ ለመዲና ሰዎች ዱቄት፣ ስንዴ፣ልብስ፣ ሽቶ እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እያመጣ ያከፋፍል ነበር፡፡ የሰሀቢዩ ቸርነት በዚህ ብቻ የሚያበቃ ነገር አልነበረም፡፡ በሚስጥር የሚያደርጋቸው ልገሳው ብዙ ነበር፡፡ ከሚጠቀሱት ውስጥ 40 ሺህ የብር ድርሃም ፣ 40 ሺህ የወርቅ ድናር፣ 200 ወቂያህ ወርቅ፣ 500 ፈረስ ለሙጃሂዶች እና 1500 ግመሎች፣ 400 ዲናር ወዘተ አበርክቷል ።

ረሱል ﷺ  ወደ አኼራ ከሄዱ ቡኋላ የረሱል ﷺ ሚስቶች በመንከባከብና በመደገፍ ከጎናቸው ቆሙ፡፡ በንግድ ያገኘውን 40 ሺህ ዲናር ለበኑ ዛህራሆች ለረሱል ﷺ ሚስቶች) እና ለድሆች አከፋፈሉ ።
ተዋወቁት አብዱረህማን ኢብኑ አውፍ ረ.ዐ ይባላል ።


💓ㅤ    📝ㅤ     🖇ㅤ   ♻️
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ
     ከዋክብቶቹ | النجوم |
❤6🥰6👌2
November 18, 2025 974 4