ይህንን ያውቃሉ ⁉️
አንድ ብቻውን የተጓዘ ብቻውን የሞተ እንዲሁም የውመል ቂያማ ብቻውን የሚቀሰቀስ ሰሀቢይ አለ ! ብቻውን የተጓዘ ማለት ፦ ሰሀቢዩ ዛሂድ ነበር ብዙ ሰዎችን መቀላቀል አይወድም እና ከዱንያ ጌጣጌጦች የራቀ ነው ። ብቻውን የሞተ ፦ ሰሀቢዩ ሜዳ ላይ ነው የሞተው ከሰዎች የራቀ በረሃ ላይ ባለቤቱና አንድ ህፃን ልጁ አብረውት ነበሩ ባለቤቱ እንደሷ ተጓዦችን ስታይ ጠርታቸው እዛው በረሀው ላይ ቀበሩት
ከቀባሪዎች ውስጥ አብደላህ ኢብኑ መስዑድ ነበረበት ። ብቻውን የሚቀሰቀስ ፦ የውመል ቂያማ ብቻውን ይቀሰቀሳል ሁኔታውም እንሚያሳየን ቦታው ላይ እሱ ብቻ ነው የተቀበረው ማለተም አሁንም በፊታም ሰው አልተቀበረበትም ። ተዋወቁት አቡዘር አልغِፋሪይ ረ.ዐ ይባላል
ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል አቡዘርን አላህ ይዘንለት ብቻውን ይጓዛል ፣ ብቻውን የሞታል ፣ የውመል ቂያማም ብቻውን ይቀሰቀሳል ።
💓ㅤ 📝ㅤ 🖇ㅤ ♻️
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ከዋክብቶቹ | النجوم |

11November 6, 2025 859 3