“ በቅርቡ ጫማ እሰቅላለሁ “ ሮናልዶ
⏩ “ አለም ዋንጫ ህልሜ አይደለም "
ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቅርቡ ጫማ ለመስቀል ዝግጅት መጀመሩን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።
“ ጨማ የመስቀያ ጊዜዬ በቅርቡ ነው “ ያለው ሮናልዶ “ ከባድ ይሆናል ያንን ሳስብ አለቅሳለሁ ነገርግን ዝግጅት ጀምሬያለሁ ብሏል።
ሮናልዶ ስለ አለም ዋንጫ ምን አሉ ?
- የአለም ዋንጫ ህልሜ አይደለም እኔን እንደ ተጨዋች ሊገልፀኝ አይችልም።
- አንድ ውድድር 6 ወይም 7 ጨዋታዎች ተጫውቼ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች አያደርገኝም እንደዛ ከታሰበ ፍትሀዊ አይደለም።
ሮናልዶ ስለ ዲያጎ ጆታ ምን አለ ?
የዲያጎ ጆታን መሞት ስሰማ ማመን አልቻልኩም ነበር ለብዙ ሰዓት አልቅሻለሁ።
- ለሀገሬ ፣ ለቤተሰቤ ፣ ለቡድን አጋሮቼ ለሁሉም ሰው በጣም አስቸጋሪ ወቅት ነበር።
ሮናልዶ ለግል ህይወቱ ምን አለ ?
- ገንዘብ እቃዎችን ለመግዛት አስፈላጊ ነው ነገርግን በህይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር አይደለም።
- ስንት መኪና እንዳለኝ በግልጽ አላውቀውም 41 ይመስለኛል ነገርግን እርግጠኛ አይደለሁም።
- በህይወቴ ከገዛኋቸው ነገሮች ሁሉ አሁንም ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሁበት ውዱ የግል ጄቴ ነው።
ሮናልዶ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ምን አለ ?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይሄንን አለም ወደ ተሻለ መለወጥ ከሚችሉ ሰዎች አንዱ ነው።

















