ሰዎች "ለምን ቸልተኛ ሆንክ?" ሲሉህ፣ ያልገባቸው ነገር ቢኖር አንተ ቸልተኛ የሆንከው በሰዎች ላይ ሳይሆን፣ ዳግም ልብህ እንዳይጎዳ እየጠበከው ስለሆነ ነው። ዓመታት የፈጀ ወዳጅነት በአንዲት ጀንበር እና በትንሽ ምክንያት ሲፈርስ ስታይ ሰው ማለት አላፊ እንግዳ መሆኑን ትማራለህ። ስለዚህ መራቅህ ሰውን መጥላት ሳይሆን፣ በሰው ላይ ያለህን ከመጠን ያለፈ ጥገኝነት ማቆምህ ነው።
ረጅም ጊዜ የገነባኸው ወዳጅነት ያለምክንያት ሲፈርስ፣ ሰዎችን በልብህ ዙፋን ላይ ማስቀመጥ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ታያለህ፣ከዛም ዙፋኑን ለራስህ ሰላም ብቻ ትተወዋለህ። አሁን የሰው ልጅን የምታየው እንደ ቋሚ የህይወትህ ማገር ሳይሆን፣ አብሮህ መንገድ እንደጀመረ እና መውረጃው ሲደርስ እንደሚወርድ ተጓዥ መንገደኛ ነው።
ለአዳዲስ ሰዎች የምትሰጠው ሌላ አዲስ እና የዋህ ልብ የለህም። ያለህ ያው የተሰፋ፣ የትላንት ጠባሳ ያለበት፣ ነገር ግን የበለጠ ጠቢብ የሆነ ልብ ነው።
አዲስ ሰወችን ስትቀበል ያለ ቅድመ-ሁኔታ ተቀበላቸው፣ ግን አትደገፍባቸው፦ አብረውህ እስካሉ ድረስ ጊዜውን አጣጥም፣ አክብራቸው፣ ውደዳቸው፤ ግን "ለዘላለም አብረውኝ ይኖራሉ" የሚል የውሸት ተስፋ አትሰንቅ።
የልብህን በር ከፊል ክፈት ወደ ህይወትህ እንዲገቡ ፍቀድላቸው፣ ነገር ግን የደስታህ እና የህልውናህ ቁልፍ አትስጣቸው።
ማንነታቸውን አክብር አንዳንዴ አዳዲስ ሰዎች የሚመጡት የድሮዎቹን ቦታ ለመተካት ሳይሆን፣ የራሳቸውን አጭር ምዕራፍ ጽፈው ለማለፍ ሊሆን ይችላል።
በስተመጨረሻም ሰው አትፈልግም ለሚሉህ ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሰዎችን አልጠላሁም፤ ሰዎችን መፈለግም አላቆምኩም። ነገር ግን በገነባሁት ልክ መፍረስን ስለደጋገምኩ፣ አሁን ግንበኛ መሆን አቁሜ ተመልካች ሆኛለሁ። ለአዲሶቹ የምሰጠው ንፁህ እና ያልቆሰለ ልብ የለኝም፤ ያለኝ የትላንት ጠባሳውን የሚያከብር እና ነገ ዳግም ላለመሰበር የሚጠነቀቅ ብልህ ልብ ብቻ ነው።
የሚመጣን በፍቅር እቀበላለሁ፣ የሚሄድን ባላየ ባልሰማ ሙድ ዝም እለዋለሁ።🚶♂
@treeplh2
@treeplh2
@treeplh2











