መልዕክት ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ::
ውድ ወላጆች የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍት የመጣ በመሆኑ ክፍያ የፈጸማችሁበትን ኦሪጅናል የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከማክሰኞ፣ ነሐሴ 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም. እስከ አርብ፣ ነሐሴ 15 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም. ድረስ ብቻ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
በተጨማሪም የተማሪዎች መታወቂያ ካርድ ተዘጋጅቶ ስላለቀ ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳጊዎች ብቻ በአካል ት/ቤት በመገኘትና በመፈረም መውሰድ ትችላላችሁ።
ጥብቅ ማሳሰቢያ:-
🔹 መጽሐፍ ለመውሰድ የከፈላችሁበትን የታተመ የባንክ ደረሰኝ ይዞ መገኘት ግዴታ ነው። በስልክ ላይ የሚታይ (Soft copy) ደረሰኝ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
🔹 የተማሪዎች መታወቂያ የሚሰጠው ለወላጅ ወይም ለህጋዊ አሳዳጊ ብቻ ነው። መታወቂያው ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ ምትክ ለማውጣት ተጨማሪ ክፍያ የሚጠየቅ መሆኑን እናሳስባለን።
🔹 ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውጪ መጻሕፍቱን ማደል ሰለማንችል፣ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ብቻ መጥታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን።
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር