በእርግዝና ወቅት አለማስመለስ የእርግዝና ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል?
አለማስመለስ ወይም የጠዋት ህመም (Morning Sickness) አለመኖር በራሱ የእርግዝና ችግር ምልክት አይደለም።
የሰውነት መለዋወጥ: የእርግዝና ምልክቶች ከሴት ወደ ሴት ይለያያሉ።
አንዳንድ እናቶች ምንም አይነት የማቅለሽለሽ ወይም የማስመለስ ምልክት ሳይታይባቸው እርግዝናቸውን በሰላም ያጠናቅቃሉ። ስለዚህ አለማስመለስ እርግዝናው ጤናማ እንዳልሆነ አያሳይም።
⚠️ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች
ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱም ሁኔታዎች በራሳቸው አስጊ ባይሆኑም፣ ከሚከተሉት ምልክቶች ጋር አብረው ከተከሰቱ ግን በአስቸኳይ ወደ ህክምና መሄድ ያስፈልጋል፦ እነዚህም
👉ከባድ የማህፀን ወይም የታችኛው የሆድ ቁርጠት
👉የደም መፍሰስ
👉የፈሳሽ መፍሰስ
👉 ከባድ ህመም ከማዞር/ራስ መሳት ጋር
ይጠቀሳሉ።
ነገር ግን የማስመለስ ስሜት አለመኖሩ ብቻ የእርግዝናው ጤናማ አለመሆኑን አያሳይም። እያንዳንዱ እርግዝና የተለየ ስለሆነ ምልክቶችም ከሴት ወደ ሴት ሊለያዩ ይችላሉ። ከላይ ከተጠቀሱት አስጊ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ካጋጠመሽ ግን በቶሎ የጤና ባለሙያ አማክሪ።
ቀጠሮ ለመያዝ 📞 096 894 5103
TenaSeb - ለሴቶች!
በ online ምክር ወይም በአካል ህክምና
ማግኘት ይችላሉ።
በስነተዋልዶ ጤና ዙርያ በብቁ ባለሞያዋች የተሟላ ህክምና ለሴቶች ይሰጣል።












