የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም ቅበላ የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም ይሰጣል።… — Temari News — TG.ME

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም ቅበላ የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች የመግቢያ ፈተና ለመፈተን በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በመሆኑም ያመለከታችሁ በሙሉ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎቹ አሳውቀዋል።

ተፈታኞች በዕለቱ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያዎች መገኘት ይጠበቅባችኋል። የሞባይል ስልክ እንዲሁም ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመልካቾች ለፈተና ስትቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የአድሚሽን ካርድ እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews
❤17👍5👏2👌2
September 4, 2026 5.7K 2 31