CampusPrep | ከዕረፍት መልስ ወደ ግቢ ለሚመለሱና ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ​ከረጅም ዕረፍት በኋላ ወደ… — Temari News — TG.ME

⚙️ #CampusPrep | ከዕረፍት መልስ ወደ ግቢ ለሚመለሱና ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች

​ከረጅም ዕረፍት በኋላ ወደ ትምህርት ገበታ መመለስ ወይም አዲስ የግቢ ህይወትን መቀላቀል ትልቅ የአእምሮና የባህሪ ቅያሬ ይጠይቃል። ብዙ ተማሪዎች የመጀመሪያዎቹን ወራት የሚያባክኑት ያለ ምንም ዝግጅት ወደ ግቢ ስለሚገቡ ነው።

​ከመግባትዎ በፊት ማስተካከል ያለብዎት 4 ወሳኝ ነገሮች፦

1⃣ የእንቅልፍ ሰዓትዎን ከአሁኑ አስተካክሉ (Sleep Cycle)
​በዕረፍት ጊዜ እስከ ሌሊቱ 8 እና 9 ሰዓት መቆየት፣ ጠዋት ደግሞ ረፍዶ መነሳት የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህንን ልማድ ወደ ግቢ ካመጡት በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ክፍል ውስጥ ትኩረት ማጣትና ድካም ይገጥምዎታል። ከመሄድዎ በፊት ከ5-7 ቀናት ቀደም ብለው መተኛትና ጠዋት በጊዜ መነሳት ይለማመዱ።

2⃣ «የመጀመሪያው ወር» ውጤትዎን ይወስናል
​በብዙ ተማሪዎች ዘንድ «የመጀመሪያው ሳምንት ትምህርት የለም» የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ አለ። እውነታው ግን ኮርስ አውትላይን (Course Outline) የሚሰጠው፣ የመምህራን የደረጃ አሰጣጥ ስልት (Grading Criteria) እና ዋና ዋና ማጣቀሻ መጻሕፍት (References) የሚነገሩት በመጀመሪያዎቹ ቀናት ነው። እነዚህን ቀድሞ የተረዳ ተማሪ ሴሚስተሩን ሙሉ በሰላም ያጠናቅቃል።

3⃣ ከማህበራዊ ህይወት ጫና (Peer Pressure) ራስዎን ይጠብቁ
​ግቢ ውስጥ የሚገጥምዎ ትልቁ ፈተና የትምህርቱ ከባድነት ሳይሆን የጊዜና የጓደኛ አመራረፅ ነው።
• ​ጊዜዎን ሙሉ በሙሉ በጨዋታ የሚያባክኑ ጓደኞች ከበቡዎት ማለት ውጤትዎ መውረዱ አይቀሬ ነው።
• ​አላማ ያላቸውን፣ ትምህርታቸውንና ራሳቸውን ማደስ የሚፈልጉ ተማሪዎችን ቀርበው ይያዙ።

5⃣ በስልክዎ ላይ የሚጠቅሙ አፖችን ይጫኑ
​ከመሄድዎ በፊት ስልክዎን ለጥናት ዝግጁ ያድርጉ፦
• ​Notion / Google Keep፦ የትምህርት ፕሮግራም እና ማስታወሻ መያዣ።
• ​Anki / Quizlet፦ ቃላትንና ቀመሮችን በ«Active Recall» ለማጠናት።
• ​Forest / Pomodoro Timer፦ በጥናት ጊዜ ከስልክ ትኩረት እንዳይበታተን የሚረዱ።

💡 የመጨረሻ ሀሳብ፦
ዝግጅት አድርገው የሚገቡ ከሆነ ግቢ አስፈሪ ሳይሆን ራስዎን የሚያሳድጉበት ትልቅ እድል ይሆንልዎታል።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews
❤37👍18👌6👏4🙏4
September 5, 2026 6.4K 8 50